ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ክለቦች አሰልጣኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፤ በእግር ኳስ ስፖርት ላይ የሚደረገው ምርመራና ቁጥጥር ቀጣይነት ባለው እና በተጠናከረ መንገድ ይካሄዳል፡፡
ቀን፡ ታህሳስ 05/2011


የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ባካሄደው የተጋላጭነት ዳሰሳ ጥናት (Doping Risk Assessment) መሰረት እግር ኳሱ ከአትሌቲከስ ቀጥሎ ለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ተጋላጭ እንደሆነ መገንዘብ ተችሏል፡፡ ለዚህም በአሁኑ ወቅት በእግር ኳሱ ስፖርት ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ገንዘብ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱ እንደ ዋና ምክንያት ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡


በመሆኑም ፅ/ቤታችን ቀደም ሲል ጀምሮ በፕሪሜርሊግ ውድድሮች ላይ እና ከውድድር ጊዜ ውጭ የስፖርተኞች የአበረታች ቅመሞች ምርመራዎችን ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለብሄራዊ ሊግ ክለብ አሰልጣኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ጉዳዮች፣ የአሰራር ስርዓቶችና የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የተጀመረው እንቅስቃሴ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *