ለዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
ህዳር 23/2013 ዓ/ም
አዳማ ራስ ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH-NADO/ 40 ለሚጠጉ ከተለያዩ የህክምና ተቋማት የተወጣጡ ባለሙያዎች በዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ዙሪያ ስልጠና በአዳማ ከተማ መሰጠት ጀመር፡፡

በስልጠና ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ሲሆኑ በንግግራቸውም ላይ አገራችን ከ 2016 እአአ በዶፒን ዙሪያ የገባችበትን ችግር በማንሳት የብሔራዊ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በማቋቋም ብዙ ተግዳሮቶችን በማለፍ አሁን ላይ ለአለም ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎችን መስራት እንደተቻለ ጠቁመዋል ። የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ በአገር አቀፍ ደረጃ በስፖርቱ ላይ ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ የተለያዩ አለም አቀፍ የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር /DCOs and BCOs /ባለሙያዎችን ማፍራት ዶፒንግን ለመቆጠር ትልቅ ሚና በመኖሩ በአራት/4/ አመታት ውስጥ የባለሙያዎችን ብዛት ከ63 ወደ 83 ለማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ጽ/ቤታችን የሚሰራቸውን የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር አድማሱን በማስፋት የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመው የዚህም ስልጠናው ዋና ዓላማም አለም አቀፍ የአሰራር ስር-አቶችን ጠብቀን የምርመራና ቁጥጥር ስራዎችን እንዲሰሩ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ሰልጣኞች በጥብቅ የስራ ስርአት ስልጠናውን መከታተል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡
በስልጠናው የዶፒንግ ታሪካዊ አመጣትና ምንንነት ፡ የአሰራር ስር- አቶችና አይነቶች :የጽ/ቤቱ ስልጣናን ተግባር እንዲሁም በጸረ አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ስራ ላይ የሚውሉ ቃላት እና የጎንዮሽ ጉዳቶች /Anti Doping Terminology and Side Effect / ዙሪያ በጽ/ቤቱ ምርመራ እና ውጤት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ባለሞያዎች ገለጻ ተደርጓል ፡፡ ስልጠናው ለአምስት ቀናት ይቆያል።
ዶፒንግን በጋራ እንከላከል!!!

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *