ለፌድራል ማረሚያ ቤት አተሌቲክስ ክለብ አትሌቶችና አሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

ቀን፡- ሐሙስ ህዳር 17/03/2013ዓ.ም
ቦታ፡-አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ አደራሽ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ ለአጋፋው ፌድራል ማረሚያ ቤት አትሌቲክስ ክለብ አትሌቶችና አሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞችና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ ፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ከ120 በላይ አትሌቶችና አሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው ፤በዶፒንግ ምንነት፤ በሚያስከትሉት ጉዳት፤የህግ ጥሰት፤በምርመራ ሂደት፤እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡

የስልጠና ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የፌድራል ማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ዋና ኤንስፔክተር ወንዶሰን ማንዳፈሮ ሲሆኑ ፤ባደረጉት ንግግር ዶፒንግ በስፖርት ዘርፉ ላይ ትልቅ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል ብለዋል፤ በመሆኑም አትሌቶች ይህን አውቀው ትምርቱን በትኩረት እዲከታሉ አሰስበው መድረኩን አስጀምረዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተዘጋጀው በጽ/ቤቱ የትምህርት፤ስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ሲሆን፤ትምህርቱን የሰጡ የጽ/ቤቱ ባለሞያዎች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በአገር ዓቀፍ ደረጃ ዶፒንግን ለመቆጣተርና ለመከላከል እዲቻል በበጀት ዓመቱ የፀረ-ዶፒንግ የግንዛቤና የህዝብ ንቅናቄ መርኃ-ግብሮችን ዘርግቶ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

የፌድራል ማረሚያ ቤት አትሌቲክስ ክለብ በ1975ዓ.ም የተቋቋመ ስፖርት ክለብ ሲሆን፤ክለቡ በርካታ አንጋፋ አትሌቶችን እንደ ኮማደር ድራቱ ቱሉ፤ፋጡማ ሮባ፤ጥሩነሽ ዲባባ፤ስለሽ ስህንና ቁጥሬ ዱለቻ የመሳሰሉ አትሌቶችን ያፈራ አንጋፋ የአትሌቲክስ ክለብ ነው፡፡

 

 

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *