በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩንቨርሲቲ በ2011 ዓ.ም ለሚመረቁ የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ጥር 18/2011 ዓ.ም

በአገራችን በስፖርት ሳይንስ ተማሪዎችን ከሚያሰለጥኑ ዩንቨሪስቲዎች በቀዳሚነት እና በአንጋፋነት በሚታወቀው በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩንቨርሲቲ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከዩንቨርስቲው የስፖርት ሳይንስ ዲፓርተመንት ጋር በመተባበር 85 ለሚሆኑ የስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ በየደረጃው የተዘረጉ የአሰራር ስርአቶች እና አደረጃጀቶች፣ የህግ ማዕቀፎች እና በተለያዩ ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በዩንቨሪስቲው አዳራሽ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡


ይህም ስልጠና በቀጣይነት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በሌሎች ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎችም ስልጠናውን ለመስጠት ጽ/ቤቱ ትኩረት ሰጦ የሚሰራ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *