በፌዴራል ፖሊስ ክለብ (ኦሜድላ) ስር ለሚገኙ አትሌቶችና አስልጣኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨብጫ ስልጠና ተስጠ፡፡
በአገራችን አንጋፋ ከሆኑት የስፖርት ክለቦች ውስጥ አንዱ በሆነው(ኦሜድላ) ስፖርት ክለብ በቀን 02/07/2012 ዓ.ም ወደ 30 ለሚጠጉ አትሌቶችና አስልጣኞች በፀረ- አበረታች ቅምሞች (ዶፒንግ) ዙሪያ በክለቡ አዳራሽ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናወ የተሰጠው በጽ/ቤቱ የትምህርት ስልጠና ባልሙያ በሆኑት በአቶ ዳንሄል ተስፋዬ እና በአቶ ሀብታሙ ካሱ ሲሆን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መስረታዊ ጉዳዮች፤ በየደረጃው ባሉ የአሰራር ስርዓቶች እና አደረጃጀቶች ፤ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ሂደት ፤የተከለከሉ የስፖርት አበረታች ቅመሞችና ዘዴዎች እንዲሁም የሚያስከተሉት ጉዳቶች በአጠቃላይ በፀረ-አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተስጥቷል፡፡
እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት ከስልጠናው ተሳታፊዎች የተጠቆመ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች የሰፖርት ማሰልጠኛ ክለቦች ስልጠናው እንደሚቀጥል ተጠቅሷል፡፡