አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢትዮጲያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የኢትዮጲያ ጸረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በመገኘት የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ ።
ቀን፡- 12/05 /2012
የጽ/ቤቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና ስራ በዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ማብራሪያ በስፋት የተሰጠ ሲሆን ተቋሙ አሁን ያለበትን ሁኔታ በሚያሳይ መልኩ በዝርዝር አቅርበዋል።
የጽ/ ቤቱ ም/ ዋ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በበኩላቸው ጽ/ቤት በአለም አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ በማመሳከር ጸረ አበረታችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀውን የህግ ማዕቀፍ አብራርተዋል።
በመቀጠል ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በፀረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዙሪያ የነበራቸውን መረጃ በዛሬው እለት ባገኙት ገላጻ እና በቦታው ባዩት ነገር ከፍ እንዳለ ገልጸዋል፡፡
ጽ/ቤቱ ያለበት ሁኔታ ከፍ ለማድረግ በተቻለ መልኩ በመንቀሳቀስ ለጽህፌት ቤቱ ችግር የሚሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሌሎች ጋር በቅንጅት እና በትትብብር መስራት መቻል እንዳለበት ተናግረዋል ።
የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የተሰጠው አላፊነት ከፍተኛ መሆኑና የኮሙኒኬሽን አግባበቡን በማሳደግ በአለም አቀፍም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ሚዲያ በመጠቀም የኮሙኒኬሽን አግባቡን በማሳደግ የአገሪቱን ገጽታን የመገንባት ጉዳይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከጽ/ቤቱ ጋር ተቀራርቦ የመስራት ክፍተት መኖሩ እና ጽ/ቤቱ ገና በመደራጀት ላይ ስለሚገኝ ስራቸዉን ተንቀሳቅሰዉ በተሻለ ደረጃ ለማከናወን የመኪና እጥረት እንዳለባቸዉም ለኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
በመጨረሻም አቶ ኤሊያስ የጽ/ቤቱን ግንዛቤ የማሳደግ ዙሪያ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ኮሚሽኑ አቅሙ በቻለ መጠን አስፈላጊዉን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።