የመልካም ምኞት መግለጫ

አዲሱ የ2013 ዓመት ንፁህ ስፖርት የሚስፋፋበትና የአገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚሳካበት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን በጽ/ቤታችን ስም እንገልፃለን፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች እምርታዊ ለውጥ (Reform) ላይ የምትገኝ ሲሆን የስፖርቱ ሴክተርም በተመሳሳይ መልኩ ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ለማለት ተቋማዊ ለውጥን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የስፖርቱን እድገት በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን መከላከልና መቆጣጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር በመሆኑ ላለፉት ጊዜያት ዘርፈ-ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በቀጣይም ይህ ጅምር እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤትም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና ከስፖርቱ ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በ2013 በጀት ዓመት ስኬታማ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተሸጋግሯል፡፡

ስለሆነም ሁሉም ስፖርተኞች፣ የስፖርቱ ማህበረሰብ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለ2013 ዓ.ም የእንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክታችንን እያስተላለፍን የበኩላችሁን ገንቢ አስተዋፅኦ ማበርከት እንድትችሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

አዲሱ አመት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እና ለስፖርቱ ማህበረሰብ የስኬትና የብልፅግና እንዲሆን እንመኛለን፡፡

መልካም በዓል !!!
የኢትዮጲያ ብሔራዊ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *