0 0
Read Time:54 Second
ሁለተኛው ዙር የስፖርት አስተዳደር ሙያ ማሻሻያ የአቅም ግንባታ ስልጠና  በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ይገኛል።
ሚያዚያ 18/2013 ዓ.ም
አዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ከኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ስልጠና ሲሆን በስልጠናው የስፖርት ማህበራት አመራሮችና ከተለያዩ የስፖርት ማሰልጠኛዎች የተወጣጡ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
መድረኩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ መልዕክት በማስተላለፍ በይፋ ከፍተውታል፡፡
የኢትዮጲያ ብሔራዊ ጸረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ስራዎችን በጋራ በስፋት እየሰራ መሆኑን በማንሳት የዚህም ስልጠና አላማ ስፖርቱን እንዴት መምራት እንዳለብን አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።
አያይዘውም ስፖርቱን ከአበረታች ቅመሞች መከላከል ይገባል ለዚህም እዚህ ያለው የስፖርት ማህበረሰብ የአበረታች ቅመሞች አስከፊነት እና የሚፈጥረውን ችግር በማወቅ መረጃዎችን በማስተላለፍ እና መተግበር ትልቅ ሃላፊነት እንዳለበት ተናግረዋል።
በዛሬውም እለት የልቦና ውቅር ለውጥ እና የስፖርት ማርኬቲንግ ምን ማለት ነው እንዴትስ ከስፖርቱ ጋር ልንሰራባቸው ይገባሉ በሚሉ ጉዳዮች በባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው ከዛሬ ሚያዚያ 18- 20/2013 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን 50 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል ስልጠናው በስፖርት አስተዳደርና አመራር ፣ በሀብት አሠባሰብና አጠቃቀም እንዲሁም በፀረ አበረታች ቅመሞች መከላከል እና በፀረ አበረታች ቅመሞች ህግ ማዕቀፍ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ ነው ።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *