የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA)፣ የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አፍሪካ ሪጂናል ቢሮ፣ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-ዶፒንግ ተቋም (SAIDS) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት የስራ ኃላፊዎች የቴሌ ኮንፈረስን በማካሄድ በአገራችን እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂዶዋል፡፡

በዚህ ውይይት ላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት የተካሄዱ ጉልህ ተግባራትን በመለየት ማቅረብ የተቻለ ሲሆን በተለይም የፅ/ቤቱን አቅም በግብዓት፣ በአሰራርና በሰው ኃይል በመገንባት፤ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ወይም ፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ስልጠና እንቅስቃሴውን በማጠናከር፤ የምርመራና ቁጥጥር ተግባራትን በማጎልበት፤ የህግ ጥሰት በሚፈፅሙ አትሌቶችና ሌሎችም አካላት ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ፤ አለም አቀፍ ግንኙነቱን በማጠናከር እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ የተመዘገቡ ውጤቶች ተገምግመዋል፡፡

በዚህም ረገድ እንደ አገር ባለፉት ጊዜያት የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ የተቻለ መሆኑን በውይይቱ ላይ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን አጠቃላይ ተሞክሮውንም በሌሎችም የአፍሪካ አገሮች የማስፋት እንዲሁም የአፍሪካ የፀረ-ዶፒንግ ፎረምን የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ(WADA) የስራ ኃለፊዎች ጠቁመዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *