የኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር የጋራ የውይይት መድርክ አዘጋጁ ፡፡
ቀን /14/01/2013 ዓ.ም
የአገራችን የስፖርት ፀረ-አበረታች እንቅስቃሴ ከየት? ወዴት?፣የፀረ-አበረታች የህግ ማህቀፍ ቅኝት እና የ2013 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ምን ይመስላል በሚሉ ጉዳች የኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል በውይይቱ ላይ ሠንድ አቅርበዋል፡፡
በሰነዱም የባለፉትን አመታት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በማለፍ በአለም አቀፍ ተሳትፎዎች ላይ ጥሩ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻል የጽ/ቤቱ ትልቅ ድል መሆኑን የጠቆሙት በቀጣይም ይህን አጠናክሮ ለመሄድ የውይይት መድረኩ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል ፡፡ በዚህም መሰረት የትህምርትና ስልጠናዎችን ከፌዴሬሽን ጋር በመሆን አጫጭር ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ግንዛቤዎችን ማስደግ ፣የዶፒንግ ጉዳይ በመሠረታዊ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ አካቶ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣ ፌዴሬሽኑ ለብሄራዊ ቡድን ስልጠናዎን ሲሰጥ የፀረ- ዶፒንግን ፅንሰ ሃሳብ እንደ አንድ ጉዳይ አድረጎ መስጠት እና በክለቦች ላይ በቂ የሆኑ የፀረ-ዶፒንግ ስልጠናዎችን መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ዳሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ከCategory “A” ምድብ ለመውጣት በብቃት መስራትና ከተቻለ በ2020 እ.ኤ.አ ካልተቻለ ግን ለ2021እ.ኤ.አ መሠረት መጣል ይኖርብናል ብለው፡፡የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) መስፈርት በአግባቡ መፈፀም ፣ለቶክዮ ኦሎምፒክ በቂ ዝግጅት ማድረግ ፣ የትምህርትና ስልጠና የህዝብ ንቅናቄ ከተለያዩ ተግባራት ጋር ማዋሀድ እና በአለም አቀፉ ደረጃ በግላቸው የሚሳተፉ አትሌቶችን የፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት መዘርጋት የ2013 ዓ.ም በጀት ዕቅድ ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸው ጠቁመዋል፡፡
በአለም አቀፉ የፀረ- ዶፒንግ ህግ ውስጥ ላይ በቀጣይ 2021 እ.ኤ.አ በአንድ አገር ላይ ለሚመዘገቡ የዶፒንግ ጥስቶ አትሌቶችን ከመቅጣት ባለፈ የአገሪቱ ፌዴሬሽኖችን መቅጣት አልፎም እስከ ማገድ የሚያደርስ የህግ አሰራር ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑንም አያይዘው የጠቆሙ ሲሆን በዚህም ጉዳይ እንደ አገር ትልቅ ስራ እንደሚጠበቅብን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስነ-ምግብ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሪት ቅድስት ታደስ የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፀረ-ዶፒንግ ዙሪያ ምን ሰራ?፣Category “A” መስፈር ቶቹ ምንድ ናቸው? እና በቀጣይ 2020 እ.ኤ.አ ዕቅድ ምን ምን ናቸው የሚሉ ጉዳዮች ላይ ሠንድ አቅርበዋል ፡፡
ወ/ሮ ፋንታዩ ገዛኸኝ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ጸረ- አበረታች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳሬክተር በበኩላቸው የቀረቡ ሰነዶች በቀጣይ ምን መስራት ይጠበቅብናል የሚሉ ነገሮችን ያሳዩ ሲሆኑ በተለይ በግላቸው ለውድድር የሚሄዱ አትሌቶች እና ኤጀንቶች ላይ የቁጥጥር ስርዓቱን በማጠንከር በአገር ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ማስቆም ይገባል ብለዋል፡፡
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እታች ድረስ በማውረድ መሰራት እንዳለበት አስታውሰው እንድ አገር ጠንከር ያለ ህግ በማውጣት በተለይ በግል የሚወዳደሩ አትሌቶች በፌዴሬሽኑ እውቅና ውድድራቸውን የማካሄድ ስርዓት እንዲኖር መሰራት እዳለበት ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ ቅንጅታዊ አስራሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት በማለት ጥምር ኮሚቴ በማዋቀር ጠንከር ያለ የሕግ ስርዓት ማዘጋጀት በተለይም ማናጀሮች ላይ ጠበቅ ያለ ህግ ማዘጋጀት አሁን ላይ ግድ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ ለዚህም አስፍላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል፡፡