የፀረ አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ባለሙያዎች (DCOs and chaperon) አቅም ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ጽ/ቤቱ አስታወቀ

ቀን፡ 01/03/2011 ዓ.ም

የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የአገራችንን ስፖርት ውጤታማነት ለማጎልበትና ጤናማ የሆኑ ስፖርተኞችን ለማፍራት በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት እየሰራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ገለፀ፡፡
በጽ/ቤቱ የስፖርት ጸረ አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም ለአራት ተከታታይ ቀናት በራስ ሆቴል ‹‹ በውድድር ጊዜ እና ከውድድር ጊዜ ውጪ›› የስፖርተኞች ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ሂደት፤የምርመራ ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት፤የምርመራ ናሙና አሰባሰብ ሂደት እንዲሁም የፓራሎምፒክ ስፖርተኞች የምርመራ ናሙና አሰባሰብ ሂደት እንዴት መካሄድ አለበት በሚሉና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለተውጣጡ የበጎ ፍቃድ የዶፒንግ ቁጥጥር ባለሙዎች(DCOs and chaperon) በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር ተደግፎ ሲሰጥ የነበረው ያቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡


በስልጠናው መክፈቻ እለት ተገኝተው ስልጠናውን ያስጀመሩት እና የጽ/ቤቱን የስራ አፈጻጸምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስመልክተው ገለጻ ያካሄዱት አቶ መኮንን ይደርሳል የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር እንዳሉት ጽ/ቤቱ የተቋቋመበትን ተልእኮ ለማሳካት እንዲችል በሰው ኃይል ልማት፣በአደረጃጀት እና የተለያዩ አሰራሮችን በመተግበር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን እንዲሁም ቀደም ሲል ተጀምሮ የቆየውን የስፖርተኞች ምርመራ እና ቁጥጥር እንዲሁም ኢንተለጀንስና ኢንቨስቲጌሽን እንቅስቃሴ በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የመለየትና የማስቀጠል ተግባራት ይከናወናል ብለዋል፡፡
አቶ መኮንን በመቀጠልም የባለሙያዎችን እውቀትና ክህሎት በተጨባጭ ለማሳደግ ሥልጠና እንዲከታተሉ ያስፈለገበት ምክንያት የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችላቸውን መሠረታዊ ዕውቀትና የአሰራር ሥነ-ምግባር እንዲጨብጡ ለማድረግ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *