ጽ/ቤቱ /ETH-NADO/ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ፤ የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በ2013 ዕቅድ ላይ ውይይት ጀመረ፡፡
የ2012 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም መልካም እደነበር ተገለጸ፤
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ቀን፤ሀሙስ መስከረም 28/1/2013 ዓ.ም
ቦታ፤ አዳማ ጀርመን ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ፤የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በ2013 ዕቅድ ላይ ከጽ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር መወያየት ጀመረ፡፡
ውይይቱ ከመስከረም28-30/2013 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፡፡ በዛሬው ዕለት የ2012 በጀት አመት እቅ ድ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል በቀረበው ሪፖርት ዙርያ ሰፊ ማብራሪያ ሰተዋል፡፡በበጀት አመቱ የተቋሙን እቅድ ከማዘጋጀት፤የትምህርትና ስልጠና፤ የህዝብ ንቅናቄ እዲሁም በየደረጃው የምርመራና ቁጥጥር በኩል ሰፊ ስራዎች መከናዎናቸው የተገለጸ ሲሆን ፤ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን፤ የቁጥጥርና የክትትል በየርከኑ ተጠናክረው እዲቀጥል በማድረግ በኩል ስራዎች በእቅድ መሰርት እተከናወኑ መቆየታቸውን ፤አለም ዓቀፍ ግኑኝ ነት የማጎልበት ስራዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ መከናወናችውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
ጽ/ቤቱ የነበረው አፈጻጸም መልካም የሚባል ሲሆን ነገር ግን በግምገማ መድረኩ ላይ የተጠቀሱ ክፍተቶችን በመድፈን በኩል ሰፊ ስራ መስራት አደሚገባው ተገልጻል ፡፡
በመጨረሻ ከመድረኩ ለተነሳው ጥያቄ የጽ/ቤቱ አመራሮች ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መኮንን ይደርሳልና ም/ ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛህኝ ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
ውይይቱ በነገው እለት የሚቀጥል ሲሆን የ10 አመቱ የስትራቴጂ እቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ፡፡