ቀን፡ 25/03/2013 ዓ.ም
ቦታ፡ አዳማ ራስ ሆቴል
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የምርመራ እና ቁጥጥር ዳይሮክተሬት አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የ DCO እና BCO ባለሙያዎች ስልጠና የቀጠለ ሲሆን የዛሬው የጥዋት የስልጠና መርሀ ግብር የሽንት ናሙና አሰባሰብ ሂደት (urine sample collection process) : ስታንዳርዱን ያልተሟላ የሽንት ናሙና አሰባሰብ ሂደትን (Partial urine sample collection process) እንዲሁም በሽትን ናሙና አሳባሰብ ወቅት የምንገለገልባቸው እቃዎችን በሚመለክቱ ጉዳዮች ላይ በጽ/ቤቱ የአትሌት ባዮሎጂካል ፓስፖርት አስተባባሪ ባለሙያ በወ/ሪት ሔለን ገ/ሚካኤል እና በሌሎች ባለሙያዎች በጋራ በመሆን በተግባር የተደገፈ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡