ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር ለመካከለኛና ረዥም ርቀት አትሌቶችና አመራሮች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም በዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በኢትዮጵያ ሆቴል ተሰጠ፡፡
‹‹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH_NADO/ ከተመሰረተ አጭር ጊዚያት ቢሆነውም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እያደደረገ ያልው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን፡፡›› አቶ ተሾመ ዘውዴ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር ቴክኒክ ዳይሬክተር ገለጹ፡፡
Ethiopian National anti-Doping office /ETH-NNADO/ on February 02, 2021, has to provide Anti-Doping Awareness Creation Training for Commercial Bank of Ethiopia /CBE/Sports club Association on the concept of doping and related issues.
60 Athletes and Administrates were in Attendance at the Training session.
(ጥር ዕረቡ 26/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሆቴል) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH_NADO/ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር ለመካከለኛና ረጅም ርቀት አትሌቶችና አመራሮች በዶፒንግና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በኢትጵያ ሆቴል አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
(ስልሳ) 60 ያህል አትሌቶች ስልጠናዉን ተከታትለውታል፡፡
በስልጠና መድረኩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርአት ላይ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እዳሉት ጽ/ቤታቸው በየደርጃው ህብርተሰቡንና በተለይም የስፖርቱን ማህበረሰብ በዶፒንግ እና በስፖርቱ ውስጥ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ዙሪያ ለማስተማር የሚያስችሉ የተለያዩ የስልጠና ፕሮግራሞች ቀርፆ፤ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ በዶፒንግና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡በቀጣይ ትምህርትና ስልጠናው ጨምሮ የምርመራና ቁጥጥር ተጠናክሮ እደሚቀጥል ም/ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸው፤ ማህበሩ ስልጠናው እንዲሰጥ ፍቃደኛ መሆናቸውና ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤የተዘጋጀውን ትምህርት በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበው መድረኩን አስጀምርዋል፡፡
በመቀጠል የኢትጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ አቶ ተሾመ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነዉም በአገር አቀፍ ደረጃ ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣተር እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር በ1976 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን እንደ አትሌት መሰረት ደፋር፣ሚሊዮን ወልዴ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔና አትሌት ገ/እግዚያቤር ገ/ማርያም የመሳሰሉ ታዋቂ አትሌቶችን ያፈራ አንጋፋ ክለብ ነው፡፡
ማህበሩ ለ2021 ቶኪዮ ኦሎምፒክ ከ5 በላይ አትሌቶችን ማስመረጥ ችሏል፡፡