ለኢትዮጲያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶችና አሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ቀን፡- አርብ ታህሳስ 9/04/2013 ዓ.ም
ቦታ፡-የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን አደራሽ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ለኢትዮጲያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶችና አሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞችና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ ፡፡
The Ethiopian National Anti-Doping Office (ETH-NADO) on December 18, 2020, has provided Anti-Doping awareness Creation Training to the Ethiopia paralympic committee, Athletes, and Supportive staff on the concept of doping and related issues.
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን ወደ 30 የሚጠጉ አትሌቶችና አሰልጣኞች ተገኝተው ተከታትለውታል ፡፡
ስልጠናው የተሰጠው ፤በዶፒንግ ምንነት፤ በሚያስከትሉት ጉዳት፤የህግ ጥሰት፤በምርመራ ሂደት፤ እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡
የኢትዮጲያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ የትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዮናስ አለማየሁ የስልጠናውን ፕሮግራም በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የዶፒንግ ጉዳይ በሁሉም የስፖርት ዘርፍ እና ስፖርተኛ ላይ በአሁን ወቅት ትልቅ ትስጋት ከመሆኑ አንጻር ይህ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ከፍተኛ ጥቅም አለው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ስፖርተኞች ይህንን በመገንዘብ የሚሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በትኩረት በመክታተል የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሰስበው መድረኩን አስጀምረዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተዘጋጀው በጽ/ቤቱ የትምህርት፤ስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ሲሆን፤ትምህርቱ የተሰጠው በትምህርት፤ስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር በአቶ ፈለቀ ዋለልኝ እና በባለሞያዎች አማካኝነት ነው፡፡
የፀረ-ዶፒንግ የግንዛቤና የህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራም በተለያዩ የስፖርተ ክለቦችና ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም በክልል የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት በ2013 በጀት አመት በስፋት እየተሰጠ ይገኛል።
ዶፒንግን በጋራ እንከላከል!!!