የኢትዮጲያ ብሔራዊ ጸረ-አበረታች ጽ/ቤት ፣ የኢትዮጲያ ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም የሌሎች የስፖርት ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞ በጋራ በመሆን በዛሬው እለት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ ፡፡

ቀን ፡- ሰኔ 19/10/2012

አገራዊ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለማሳካት ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተመራጭ የሆኑ ቦታዎችን በመምረጥ በካፍ እግር ኳስ ስፖርት አካዳሚ የችግኝ ተከላ የተደረገ ሲሆን የኮቪድ 19 በሽታን ለመቆጣጠር የስፖርቱ አካላት ያደረግናቸውን ጥረት በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ላይ በመድገም የተከልናቸውን ችግኞች መንከባከብ እንዳለብን በእለቱ መልዕክት ተላልፏል፡፡

ይህ መርሃ ግብር በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግንቦት 28/ 2012 የተጀመረው አገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሲሆን በዘንድሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የ5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ መያዙ ይታወቃል:;

Previous post አትሌት እታፈራሁ ተመስገን ወዳጆ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን መጠቀሟ የ12 ዓመት ቅጣት ተጥሎባታል።
Next post ጽ/ቤታችን /ETH-NAD0/ ከኦሮሚያ ሰፖርት ኮሚሽን ጋር እና ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የጋራ /partnership/የስምምነት ውል ተፈራረመ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.