የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር ባደረጉት ውይይት መደሰታቸውን ተናግሩ ፡፡
መንግስት የኢትዮጲያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤትን አደረጃጀት በመደገፍና ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ መስራት መቻሉን እንዲሁም የኢትዮጲያ መንግስት በፀረ-ዶፒንግ ዙሪያ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በዛሬው እለት ሰፋ ያለ ውይይት ያድርጉ ሲሆን በቀጣይ በአለም አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ሊያደርጉት ባሰቡት አጠቃላይ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴ እቅድ እና አገራችን ኢትዮጵያ ሊኖራት በሚገባው አለም አቀፍ ተሳትፎ ወይም ድርሻ ዙሪያ በስፋት መክረዋል ።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *