በምርመራ ቋት ለተካተቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የጎዳና ላይ ሩጫ ተወዳዳሪዎች በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

‹‹ አንጋፋ አትሌቶች እራሳችንን ከአበረታች ቅመሞች በማራቅ ፡፡ ለተተኪ አትሌቶች ሞዴል መሆን ይጠበቅብናል፡፡›› አትሌት ቀነኒሳ በቀል

በአበረታች ቅመሞችና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለሁለት ቀን ስልጠና በምርመራ ቋት()ውስጥ ለተካተቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የጎዳና ላይ ሩጫ ተወዳዳሪ አጋፋና ታዋቂ አትሌቶች አበረታች ቅመሞች በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ተሰጠ፡፡

ከህዳር 29እስከ30/2019ዓም በአዲስ አበባ ቸረችል ሆቴል የተካሄደው የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ የኤአዩ ጎዳና ሩጫ ኢንቲግሪቲ ፕሮጀክት ላይ በምረመራ ቋት ውስጥ የተካተቱ የአለም ደረጃ ጎዳና ሩጫ ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች የኤአዩ ስልሚያያቸው ጉዳዮችና ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እዲሁም አበረታች ቅመሞች በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የአትሌቶችን ግንዛቤ ማሳደግ እደሆነ በዚህ ወቅት ተገልፃል፡፡
ስልጠናው ያድራሻ ማሰወቂያ መነገዶች፤ ከውድደር ወጭ የሚሰሩ ምርመራዎች ለኤአዩ የምርመራ ፕሮግራም ዋና ማዕከል መሆናቸው፤ በምርመራ ቋት ውስጥ የገቡ አትሌቶች ማወቅ የሚገባቸው ጉዳዮችና በሌሎች ተያያዥ ርዕሶች አትሌቶች የበለጠ እዲገነዘቡት ተግባራዊ እንዲሁም የተጠያቂነትና የሃላፊነት መንፈስ የተላበሱ እዲሆኑ የሚደረገውን ጥረት እደሚያጎለበት ተመልክቷል፡፡
በተጨማሪ ዶፒንግን የሚመለከት ጉዳዮችን ሪፖርት ማድረግ ለአብነት ጉቦ ወይም ሙስና መፈጸም፤ማጭበርበር፤ ትኮሳዎች፤ ወሲባዊ ትኮሳዎች ጭምር ያልተገባ ስነ-ምግባር ሪፖርት ማድረግ ለሁሉም ፍትህዊ የሆነ የውድደር ሜዳ እዲፈጠር ጉልህ ሚና መጫወት እዲቻል፤እነዚህም ተግባራት ለዶፒንገ ህግ ጥሰት የሚያጋልጡ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በስልጠናው ፕሮግራመ ላይ ከ150 በላይ አንጋፋና ታዋቂ አተሌቶች፤ አስለጣኞችና ማናጀሮች የተገኙ ሲሆን ከነዚህ መሀከል አትሌት ቀነኒሳ በቀለና ገነዘቤ ዲባባ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

አትሌት ቀነኒሳ በቀል በስልጠናው ላይ በሰጠው አስተያየት አጋፋ አትሌቶቸች ለተተኪ አትሌቶች ሞዴል በመሆን አላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅብናል፡በቅድሚያ እራሳችን ንህጹ ሆን በመገኘት ነው ለሌሎች ሞዴል መሆን የምንችለው በማለት መልክቱን አስተላልፏል፡፡