በ39ኛው ጃን-ሜዳ ሃገርአቋራጭ ውድድር ላይ የፀረ-ዶፒንግ የቅስቀሳና Outreaching ፕሮግራሙ ተካሄደ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን (ETH-ADA) ለ39ኛ ግዜ የካቲት 06/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተከሄደው የጃን – ሜዳ እና የምስራቅ አፈሪካ ኢንተርናሽናል ሃገር አቋራጭ ውድድር ላይ ለተሳተፉ የስፖርተኞችና የስፖርት ባለሞያዎች እንዲሁም የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም አካሂደዋል፡;
በዚህ ውድድር ላይ የተለያዩ የቅስቀሳና ፕሮሞሽን ማቴሪያሎች ፤ ብሮሸሮች ፣ የፊት ማስክዎች፤ ለስፖርተኞች ፣ ለስፖርት ባለሞያዎች፣ለስፖርት አመራሮችና ሌሎችንም ተሳታፊዎች የተሰራጨ ሲሆን በተለይ አሳታፊ የሆኑ፤አትሌቶችን በቀላሉ ግንዛቤ እዲጨብጡየሚያስችል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል በተጨማሪ የተለያዩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ባነሮች ተዘጋጅተው ለዕይታ በሚያመች ቦታዎች እዲሰቀሉተደርጓል::
በውድድሩ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት፤ከክልል፤ ከተማ አስተዳደሮች፤ ከክለቦች፤ ከዩኒቨረሲቲዎች፤ ከአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፤ ከተቋማትና የግል ተወዳዳሪዎች የተውጣቱ በርካታ አዋቂ እና ወጣት አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡

By Ermias