የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ ለኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የጋራ የውይይት መድረክ አካሄዱ፡፡
በቀደምት አትሌቶቻችን በአለም አቀፍ ደረጃ የተገነባው የኢትዮጵያ መልካም ገፀታ ማስቀጠል እንፍልጋለን ፡፡ ወ/ሮ ሳሚያ አብደላ የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
(መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ)፤ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ ለኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የጋራ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
የጋራ መድረኩ ዓላማ አጠቃላይ በፀረ-ዶፒንግ ዙሪያ በክልልና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች የጋራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፤የክልል አመራሮች አዲስ ስለሆኑ ጋራ መግባባት ለመፍጠር እና ክልሎች ያሉበትን ደረጃ መለየት ነው፡፡
በውይይቱ ወቅትም ለክልሉ የስፖርት አመራሮችና ባለሞያዎች ስለ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን አደረጃጀትና እየተሠሩ ስላሉ ሥራዎች እንዲሁም ከክልሉ ጋር በቅንጅት በሚሠሩ ስራዎች ላይ በዋና ዳይሬክተሩ በክብር አቶ መኮንን ይደርሳል ገለፃና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡
በገለፃቸው ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት የተካሄዱ ጉልህ ተግባራትን በተለይም ነ የባለሥልጣኑ መስሪያ ቤቱን አቅም በግብዓት፣ በአሰራርና በሰው ኃይል በመገንባት ጠንካራ ተቋም መፍጠር የተቻለ መሆኑን ፤ የህግ ማዕቅፎችን ማዘጋጀትና ወደ ትግበራ ማስገባት፤ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ወይም ፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ስልጠና እንቅስቃሴውን በማጠናከር፤ የምርመራና ቁጥጥር ተግባራትን በማጎልበት፤ የህግ ጥሰት በሚፈፅሙ አትሌቶችና ሌሎችም አካላት ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ፤ አለም አቀፍ ግንኙነቱን በማጠናከር እና በመሳሰሉት ጉዳዮችውጤታማ በሆነ መንገድ መፈፀም መቻሉን አብራርተዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እደክልል በፀረ-ዶፒንግን ጉዳይ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እደሚገኝ የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሳሚያ ገለፀው፤የዶፒንግ ጉዳይ የሚከታተል ባለሙያ በቡድን ደረጃ ማደጉን፤ተደራሽነቱን ለማስፋት ባለሞያ አሰልጥነን ትምህርት እንሰጣለን፣በጣም እንሰራበታለን፤የፀረ-ዶፒንግን ጉዳይ በመደበኛ ካሪኩለም ውስጥ አካቶ ለማስተማርም ከትምህርት ሚኒስትር በጋራ እንሰራለን ብለዋል፤ በቀደምት አትሌቶቻችን በአለም አቀፍ መደረክ ተገነባውን የኢትዮጵያን መልካም ገፀታ ማስቀጠል እንፍልጋለን ብለዋል፡፡
የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሳሚያ አያይዘው እደተናገሩት የምንሰራው የጋራ ነው፡፡ለእኛ ትልቅ ግባት ነው የሰጣችውን፤ እኛ ነበርን ወደናተ መምጣት የነበረብን፤እናንተ ወደኛ ስለመጣችው እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳልል እደተናገሩት ኦሮሚያ ክልል የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን በመጀመርና በመፈጸም የመጀመሪያው ነው፤ እደ ፌድራል ተቋምነታችን በጣም ጠቃሚው ነገር በቅንጅት መስራት ነው፡፡ እደአጠቃላይ ጅምር እቅስቃሴው ጥሩ ነው፤ ወደ ውጤት ቢቀየር ፤የምንደግፈው ስራ ካለ እናግዛለን፤ በቀጣይ በውጤት እንገናኛለን ብዬ እገምታለው ብለዋል፡፡
በውይይቱ ፕሮግራሙ ማጠቃለያ ሁለቱም አካላት ችግሩ የጋራ በመሆኑ የጋራ መፍትሄ እደሚያስፈልገው መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ባለሥልጣኑ ለሀረሪ፣ለሱማሌ፤ለቤኒሻንጉል፣ለጋቤላ ክልልዎችና ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮዎች የጋራ ውይይት መድረኮች ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

By Ermias