የስፖረት አካዳሚና ማሰልጠና ተቋማት አሰለጣኞች ስለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ግንዛቤ ማስጨበጥ አደሚገባቸው ተገለፀ፡፡

ፀረ-ዶፒነግን የሚመለከቱ ጉዳዮች በተለያየ ደረጃ በትምህረትና ስልጠና ካሪኩለም ውሰጥ እዲካተቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ጽ/ቤቱ ገለፀ፡፡

ዕረቡ፡-ህዳር 10/2012 ዓ.ም
አዳማ ከተማ ኮንፈርት ሆቴል

የሰፖረት ማሰልተኛ ተቋማትና አሰለጣኞች ስለሰፖርት አበረታች ቅመሞች ጉዳይ በስልጠና ካሪኩለም ውስጥ አካተው ማስተማር አደሚጠበቅባችው፤የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሚገባ መወጣት እደሚኖርባቸው አቶ መኮንን ይደርሳል የጽ/ቤቱ ዋና ዲሬከተር ገለፁ፡፡
አቶ መኮንን የህን የገለፁት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ- አበረታች ቅመሞእ ጽ/ቤት ለስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኞች በፀረ-ዶፒንግ ፅንሰ ሃሳብና የአሰራር ስርአቶች ዙሪያ ከህዳር 9-10/2012 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ላይ ለተሳተፊ ሰልጣኞች ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ነው፡፡

ዋና ዲሬክተሩ በማያያዝም የጽ/ቤቱ ዋና ዓላማ ራዕይና ለራዕዩው ዕውን መሆን የሚበጀውን ሰትራቴጂ ነድፎ በመቀሳቀስ ላይ መሆኑን አመልክተው የታቀደውን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ ክተለማቸው ስልቶች መካከል በአገራቀፍ ደረጃ የስፖርት ማሕበራትን፣ክልሎችን፣እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በመደገፍ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴ የማስተባበር ተግባራት ማከናወን መሆኑኑ ጠቅሰው፡፡

በዚህ መሰረተ ሃሳብ መነሻነት የስፖርት ማሰልተኛ ተቋማት አሰልጣኞችን በፀረ-ዶፒንግ ምንነትነና ተያያዥነት ስላላቸው ጉዳች መሰረታዊና በቀጣይ ስራቸው እግዛ የሚያደርግላቸውን ግንዛቤ እደጨብጡ ዋና ዲሬክተሩ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
በተያያዘ የጽ/ቤቱ የስፖርት አበረታች ቅመሞቸችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ እደሚካተቱ ከትምህረት ሚኒስተር ጋር በጋራ እየሰራ እደሆን፤ባአብዛኛው ሥራው መጠናቀቁን ዋና ዲሬክተሩ አረጋግተዋል፡፡

ክትናንትናው የሰልጠና መርሃ ግብር የቀጠለው በስፖርት የሚወሰዱ ድጋፍ ሰጭ ምግቦች(supplements)ምንንት፣አጠቃቀሙና ስጋቶቹ ፤ባግባቡ ለመጠቀም ምን ይጠበቃል እዲሁም ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ከዶፒንግ ጋር ያላቸው ዝምድና በሚል ርዕስ ዙሪያ በአትሌቲክስ ፌድሬሽን የአትሌቶች የጤና፣የስን -ምግብና የፀረ-ዶፒንግ ከፍተኛ ባለሞያ የሆኑት በወ/ሪት ቅድስት ታደሰ ሰፊና ዘርዘር ያል ገለጻ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በለቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በአዳማ በተካሄደው ስልጠና ላይ 35 ስልጣኞች የተሳትፉ መሆኑ ታወቋል፡፡