የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዶፒንግን በመክላከልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን የዓለም አትሌቲክስ የአትሌቶች ኢንቲግሪቲ ዩኒት(ኤአዩ) የበላይ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡

ሰኞ ህዳር 29/2012 በአዲስ አበባ ቸርችል ሆቴል የኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ፤የአለም አትሌቲክስ የአትሌቶች ኢቲግሪቲ ዩኒት(AIU)እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ለሚዲያ አካላት በጋራ ባዘጋጁት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የአለም አትሌቲክስ ኢንቲግሪቲ ዮኒት(AIU) ምክትል ኃላፊ ሚሰተር ቶማስ ካፕዴቪል እደገለፁት ጽ/ቤቱ ውጤታማ ስራዎች ማክናወኑንና በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እደሚገባው አመልክተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዲሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል እደተናገሩት የኤአዩ(AIU) ጎዳና ሩጫ የአበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ፕሮግራሙን ጽ/ቤቱ እደሚደግፍ ስራውንም ለማከናውን ቁርጠኝነት እንዳለው፡፡ፕሮግራሙን ለማስጀመር በኤአዩ(AIU) በመመረጣችን እጅግ ደሰተኞች ነን ብለዋል፡፡ የምንወደዉን ስፖርታችን ንፁህ በሆነ መንገድ ፤ፍህታዊ የስፖርት ውድድር እዲሰፍን፤ ጽ/ቤቱ ዶፒንግን ከመስረቱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የትምህርትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፤ የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ፕሮግራሞች እዲሁም የተለያዩ የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኤአዩ(AIU) የጎዳና ሩጫ ኢንቲግሪቲ ፕሮግራም ከመቶ ሃምሳ በላይ ለሆኑ በምርመራ ቋት ለተካተቱ(RTP) የአለም ደረጃ የጎዳና ላይ ሩጫ ተሳታፊዎች ፤ማናጀሮችና አሰለጣኞች በጸረ-ዶፒንግ ዙሪያ ከኤአዩ (AIU) በመጡ ባለሞያዎች ሰልጠና ተሰጥቷል፡፡ በዚ ስልጠና ላይ አትሌት ቀነኒሳ በቀለና አትሌት ግንዘቤ ዲባባ ጨምሮ ታዋቂና ስም ያላቸው አትሌቶች ማናጀሮችና አሰለጣኞች ተግኝተዋል ፡፡ስለጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተሰጥቷል፡፡

ኤአዩ ፍህታዊ የመወዳደሪያ ስፍራ ለመፍጠር የተቋቋመ ክፍል ሲሆነ ከሚያያቸው ዘርፈበዙ ጉዳዮች መካከል፤- የፀረ -ዶፒንግ እንቅስቃሴ፤ የውድድር ስርአትን የሚያደናቅፍ ክስተት ወይም ማጭበርበር፤የውርርድ የህግ ትሰቶች፤የእድሜ ማጭበርበር፤ትንኮሳ ፤ወሲባዊ ትንኮሳን ጭምሮ ጉቦና ሙስና፤ከሌላ ሀገር ዜግነት ከመቀየር ጋር በተያያዘ ማጭበርበር የሚከታተል እራሱን የቻለና ገልተኛ ተቋም ነው፡፡