የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጋር ለሚዲያ ባለሞያዎች በጋራ በመቀናጀት ያዘጋጁት የፀረ-ዶፒንግ የጋራ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ቀን፡-ታህሳስ 17/2012 ዓ.ም
ታ፡- ሄልዝ ኢንተርናሽናል ሆቴል አዳማ ከተማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ -አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት (ETH-NADO) በአገራችን ንህፁ ስፖርት በማስፋፋትና ጤናማ ተተኪ አትሌቶችን በማፍራት በአለም አቀፍ ደረጃ የአገራችንን ውጤታማነት ለማጎልበት፤የዜጎችን ሁለንተናዊ ጤንነት ለመጠበቅ ባሳለፋቸው 3 ዓመታት በየደረጃው ዘርፈ ብዙ ጠረቶች በመደረግ ላይ መሆናቸው ተገለፀ፡፡

አቶ መኮንን ይደርሳል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዲሬክተር በአበረታች ቅመሞች ጽነስ ሃሳብና በአሰራር ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከታህሳስ 17 እስከ 18 2012 ዓ.ም ለሚዲያ ባለሞያዎች ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በጋራ በመቀናጀት ለሁለት ቀን ባዘጋጀው የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አገራችን አበረታች ቅመሞች ጉዳይ ችግር ውስጥ የገባችበት ወቅት እደነበር አሰታውሰው ይህን ችግር ለመቅረፍ በአለፉት ግዚያት በርካታ ተግባራት ስሰራ ቆይተናል፤ሚዲያዎችም በአግባቡ መረጃዎችን ከማድረስ አንፃር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ባለፉት 3 ዓመታት ላደረጋችዉት አስተዋፆምስ ምስጋና የገባችዋል፡፡ በቀጣይም ከመገናኛ ብዙሀን/ሚዲያ ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ በተለይ ሚዲያዎች መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የማድረስና የማነቃት ስራ መስራት የሚጠበቅባችው ይሆናል፡፡

የዛሬው የውይይት መድረኩ አቅም የመፍጠርና ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡ በቀጣይ ከጋዜጠኞች ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል ዋና ዲሬክተሩ አቶ መኮንን ይደርሳል በተጨማሪም የሚዲያ ፎረም ተቋቁሞ ወደተግባር ተገበቷል፡፡ መረጃ የመስጠትና የመደገፍ ስራ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል፡፡

በመቀጠል በአቶ ክፍሌ ሰይፈ በጽ/ቤቱ የትምህረት/ሰ//ምር/ዳሬክቱሬት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ፅንሰ ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት ሰነድ ላይ ገለጻ ያቀረቡ በገለፃቸውም የአበረታች ቅመሞች ምንነት፤ በተዘረጉ የአሰራር ስርአቶች፤ የህግ ጥሰቶች፤ በሚያስከትሉት ጉዳቶችና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በሚሉ ዋና ዋና ሀሳቦች ላይ ሰፊና ዘርዘር ያለ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

በዚህ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ውይይት መድረክ ከ60 በላይ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መድረኩ ከምሳ በኃላ የሚቀጥል ሲሆን በመርሃ ግብሩ መሰረት በቀረበው ሰነድ ላይ የብድን ውይይት ይካሄዳል፡፡