የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሸን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት እና ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጋር በመተባባር ለስፖርት ጋዜጠኞች ባያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተጠናቋል ::
በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የጋዜጠኞች የውይይት መድረክ ሲጠናቀቅ በስፖርት ዘገባ ልምድና በጋዜጠኞች ሙያዊ ስነ-ምግባር ዙሪያ የተዘጋጀ ጽሑፍ በክቡር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጲያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ቀርቧል::
የስፖርት ጋዜጠኝነት አጀማመር ፤ የመገናኛ ብዙሃን እና የሚዲያ ባለሙያዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ሊኖራቸው የሚገቡ ድርሻ ምን መሆን አለበት ፤ በዘገባ ወቅት ሊኖሩ የሚገቡ የቋንቋ አጠቃቀም ፤ የመገናኛ ብዙሃን ዝርዝር ዓላማዎች ፤ የመገናኛ ብዙሃን ሊኖሯቸው የሚገቡ አመቺ ሁኔታዎች እና ያሉባቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር ግንዛቤ መፍጠር በሚያስችል መልኩ ስልጠና ተሠጥቷል ::
በመጨረሻም የቀረበው ጽሑፍ መነሻ በማደረግ የጋራ ውይይት ተደረጎባቸው የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል ።