በጽ/ቤቱ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር ቀጣይ ሥራዎችን ለማሳካት ሰራተኛውና አመራሩ ሊረባረብ እደሚገባ ተገለጸ፡
‹‹በቀጣይ 6 ወር የጽ/ቤቱ ዋናኛ አጀንዳ 2021 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶች ላይ ነው››፡፡ ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር
ቀን፡ ቅዳሜ የካቲት 13/2013 ዓ.ም አዳማ ኤግስኪዩቲቭ ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH-NADO/ የ2013 6 ወር የስራ አፈጻጻም ግምገማና የቀጣይ ዕቅድ ላይ ከሰራተኞችና አመራሮች ጋር ከየካቲት 12-13/2013 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ፡፡
የ2013 የስድስት ወር ዋና ዋና ግቦች የስፖርት አበረታች ቅመሞች ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቀመጠውን እቅድ ታሳቢ ያደረገ እና የትምርት፣ስልጠና እና የህዝብ ንቅናቄ፤ምርመራና ቁጥጥርና አለም ዓቀፍ ግኑኝነትን ለማጠናከር ታስበው የተነደፉ እደነበር ውይይቱን የመሩት የጽ/ቤታች ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል ገልጸዋል፡፡
ጽ/ቤቱ የያዛቸው ዕቅዶች ፋይዳቸው ትልቅ ነው፤ ያሉት ዋና ዳይሬከትሩ ቀደም ሲል የታዩ ጠሩ ጎኖች በማጎልበት እና ደካማ ጎኖችን በመፈተሸ ሰራተኛውና ባለድርሻ አካላት ለላቀ ውጤት መትጋት እደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ በ2013 የአንደኛው መንፈቀ ዓመት ጽ/ቤቱ ያቀዳቸውን ተግባራት ለመፈጸም ከፍተኛ ጥረቶችን ያደረገ ሲሆን የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ የዓመቱን እቅድ በአብዛኛው ያሳካ ሲሆን በሁለተኛው መንፈቀ አመት አቅሙን በአዲሱ አደረጃጀት /መዋቅር አጠናክሮ የተሻሉ ስራዎችን ለማከናወን ራሱን እያዘጋጀ መሁኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የተገኘው አበረታች ጅምር እንቅስቃሴ ሊመጣ የቻለው ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ ሆኖ ሳይሆን ፈታኝ ሁኔታዎች እደነበሩ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጠዋል፡፡ ለስራው የሚሆን ተሸከርካሪ አለመኖር፤ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፤ የውጭ አገር ግዥ አሰራር ችግሮችና የበጀት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በዋናነት የተስተዋሉ ችግሮች መሆናዎችውን ጠቁመዋል፡