‹ኢትዮጵያ ዶፒንግን በመከላከል ንፅህ ሰፖርት ለማስንፋፋት እያደረገች ያለው ጥረት ፤በአፍሪካ ደረጃ ሞዴል መሆን
የሚችል ተግባር መሆኑን ፡፡›› የዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ /WADA/ ፕሬዝዳት ዊቶልድ ባንካ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ በዘላቂነት የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በመከላከል ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት ትኩረት
ሰጥታ እየሰራች መሆኑን የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢሊያስ ሽኩር ተናገሩ፡፡

ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት ከዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ዊቶልድ ባንካ ጋር በበይነ መረብ ውይይት ላይ ነው፡፡
በዚህ የጋራ ውይይት ላይ ኮሚሽነር ኢሊያስ ሽኩር ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፉ ሲሆን፤ የኢፌድሪ መንግስት የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን ከመላከልና ንፁዕ ስፖርት ለማስፋፋት ያለውን ከፍተኛ ትኩረትና ቁርጠኝነት አብራርተዋል፡፡

በውይይቱ የአለማቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ /WADA/ ፕሬዝዳንት ዊቶልድ ባንካ እደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይንም ዶፒነግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ የሚደነቅ መሁኑን አመልክተው፤ የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሊሆን የሚችል መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ የዓለም አቀፉን የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴ ቀጣይ 5 ዓመት ስትራቴጂክ ትኩረት መስክ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፡፡
ኢትዮጵያ በዶፒንግ ላይ የጀመረችዉን እቅስቃሴ በማጠናከር፤ በቀጣይ የአለም አቀፉን የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ 5 ዓመት
ስትራቴጂክ ዕቅድ ተግባራዊ በማድረግ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር እድትሆን ጥረት ይደረጋል ሲሉ ኮሚሺነር ኢሊያስ ሽኩር ገልጸዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *