ለታዋቂ እስፖርተኞች፡ ለአትሌት ማናጀሮችና ተወካዩች በስፖረት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ሰልጠና

ተሰጠ!

ቀን 29/05/2011 ዓ.ም ጌትፋም ሆቴል

የኢትዩያጵያ ብሔራዊ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚወዳደሩ ታዋቂ ሰፖረተኞች እዲሁም ለአትሌት ማናጀሮች ችና ተወካዩች በነበራቸው አቅም ላይ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር የዕውቀትና የክህሎት ሰልጠና ክጥር 29/2011ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ጌትፋም ሆቴል መሰጠት ተጀመረ፡፡


የአቅም ግንባታው በዋናነት የሚያተኩረው “በምርመራ እና ቁጥጥር፣ የግል አድራሻ ምዝገባ (Whereabouts Information)፣ በውጤት አስተዳደር እና የአስተዳደራዊ ዳኝነት ስርአት(Disciplinary Hearing Procedure)፣ አትሌቶች የሚኖራቸውን መብት እና ግዴታዎች ጨምሮ በየእርከኑ ተዘርግተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ በሚገኙ የአሰራር ስርአቶች ዙሪያ” ከግንዛቤ ባለፈ ያላቸውን ዕውቀት ማሳደግ በማስፈለጉ እንደሆነ የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መኮንን ይደርሳል ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡት የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል እና በጽ/ቤቱ ከፍተኛ የአይ ሲ ቲ (ICT) ባለሙያ በሆኑት በአቶ አህመድ ሙሉጌታ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ወደ ዋናው ስልጠና ሲገባ በሰልጣኝ ተኮር የስልጠና (Learner Centered Method) ተግባራትን የሚያሳይ መርሀ ግብር በመንደፍ ነው፡፡
በመጀመሪያው የስልጠናው መርሀ ግብር የሚሳተፉ ሰልጣኞች ብዛት 29 ሲሆን ፤ 12 ሴት እና 17 ወንድ ታዋቂ ስፖርተኞች፣ የአትሌት ማናጀሮች እና ወኪሎች ናቸው፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *