Loading...

ራዕይ

በአገራችን በየደረጃው ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ነፃ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞች ተፈጥረውና ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ተወዳድሮ የማሸነፍ ባህል ጎልብቶ ማየት፡፡

ተልዕኮ 

በአገራችን በየደረጃው ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ነፃ የሆነ ስፖርት እንዲስፋፋ እና በትክክለኛው መንገድ ተወዳድረው ውጤታማ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞች እንዲፈሩ ማስቻል፡፡

የጽ/ቤቱን ቦርድ ይተዋወቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች   ጽ/ቤት በቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ የተደራጀ ሲሆን ለጽ / ቤቱ ውጤት እና ውጤታማ አፈፃፀም ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል ፡፡ ቦርዱ ሊቀመንበሩን ጨምሮ በውስጡ 7 (ሰባት) አባላት አሉት፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች   ጽ/ቤት የቦርድ አባላት

ስልጣን እና ተግባራት

የፀረ-አበረታች ቅመሞች ሕጉን ጨምሮ ከዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ሕጎችና ደንቦች ጋር የተጣጣመ እና በየደረጃው ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፖሊሲ እና የማስፈፀሚያ ስትራቴጅ በማዘጋጀት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤ በየደረጃው ህብረተሰቡንና በተለይም ደግሞ የስፖርቱን ማህበረሰብ በዶፒንግ እና በስፖርቱ ውስጥ በሚያስከትላቸው ጉዳቶች ዙሪያ ለማስተማር የሚያስችሉ የተለያዩ የሥልጠናና የግንዛቤ መፍጠሪያ ፕሮግራሞችን ይቀርፃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤ በዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ በየጊዜው ማሻሻያ...