በኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት እና በኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡
ቀን፡- መጋቢት /07/2012 ዓ.ም
ቦታ ፡- የኢ/አ/ፌ
በጋዜጣዊ መግለጫው በፀረ-ዶፒንግ ጉዳይ ላይ ኢትዮጲያ category “A” ላይ ትግኛለች ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና አጠቃላይ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት እንቅስቃሴን በሚመለከት የጽቤቱ ዋና ዳሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ለጋዜጠኞች ገለፃ አድርገዋል ፡፡
በገለፃው የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (IAAF) ወይም የአሁኑ የአለም አትሌቲክስ (World Athletics) ባወጣው የስፖርት አበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ ኢትዮጲያ በደርጃ “A” መመደቡዋ የሚታወቅ ሲሆን ይህም የሆነበት ሂደት አስርድተዋል፡፡
Category “A” ምድብ ውስጥ ለመግባት በአለም አቀፉ ደረጃ በሚዘጋጅ ውድድሮች ላይ በተለይም በአለም ሻምፕዮና በተለያዩ የጎዳና ውድድሮችና በሌሎችም የ( IAAF) ውድድሮች ላይ ያላት ተሳትፎና ደረጃ ከፍተኛ በመሆኑና በሪጅስተር ቋት ውስጥ ብዙ አትሌቶች የተመዘገቡ በመሆኑ የስፖርት ቅመሞች ያሉበት ደረጃ ትኩርት በማግኘታቸው በዚህ ደረጃ ለመግባት በመስፍርትነት ለመጠቀም መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት ኢትዮጲያ በአለም አቀፉ የጎዳና ውድድር ላይ በ ከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ የሆኑ አትሌቶች በመኖራቸው ምድብ “A” category ውስጥ ልትካተት መቻልዋን ገልፀዋል፡፡ ይህ መስፈርት ሲወጣ ካለን የተሻለ ውጤት ላይ ተመስርቶ ጥበቅ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ትኩርት ለመስጠት እንድተደረገ ገልጸዋል፡፡
 በተጨማሪም ምድብ “A” category ውስጥ መግባት ማለት በዶፒንግ የመጠርጠር ጉዳይ ሳይሆን የምንስራበትን ስርዓት ጥራት ባለው መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ ስለተፈለገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የሚዲያ አካላት ያለውን መረጃ ከኢትዮጲያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ጋር በመቀራረብ ትክክለኛ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ግልጽ የሆነ መረጃ በህብርተስቡ ዘንድ እንዲኖር ማድርግ ብንችል ያሉ ሲሆን ፡፡በመጨረሻም በፀረ -አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ዙሪያ በ2019 እ.ኤ.አ የተመዘገቡ ውጤቶችን በ2020 እ.ኤ.አ በማስቀጠል ቀጣይነታቸው ተረጋግጠው መሄድ እንዳለባቸውና ስራችንን ለቅመን በመስራት በቀጣይ የቶኪዮ ኦሎምፒክ የተሻለ ውጤት እንድናስመዘግብ የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው በማለት አሳስበዋል ፡፡
በኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኮሮናን ቫይረስን በሚመለክት ፌዴሬሽኑ እያደረግ ባለው እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቶዋል፡፡