በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ አስተደደር ስር ለሚገኙ ለአትሌቲክስ ክለብ አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጣና ተሰጠ ፡፡
ሰኞ ፣ ሚያዚያ 03/2014 ዓ.ም
ሰበታ ከተማ
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ ለአትሌቶችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችና አደረጃጀቶች፤ በህግ ማዕቀፎች እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በሰበታ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እደተናገሩት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ተደራሽ ለማድረግ እና ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እደሚገኝ ተናግረው በአጭር ጊዚም አበረታች ዉጤት ማስመዝግ እደተቻለም ገልፀዋል፡፡
የስልጠና መድረኩ ዋና ዓላማ የስፖርቱ ማህበረሰቡ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጉዳዮችን፣ጉዳቱን፣ሕግና ደንብን በአግባቡ አውቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና ሌሎችንም እንዲያሳውቁ እድል ለመፍጠር ነው ብለዋል ።
የሰበታ ከተማ አስተደደር ወጣቶችና ስፖርት ቢ ከኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መድረክ ላይ 90 የሚሆኑ የማርሻል አርትስ፣ የጅምና ስቲክስ እና የመረብ ኳስ አትሌቶችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

By Ermias