ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ባከናወናቸው ስራዎች ዙሪያ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ሐምሌ /25/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በ2016 በጀት አመት በአበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ያከናወናቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ ለፓሪስ ኦሊምፒክ ቅድመ ዝግጀት እና የአበረታች ቅመሞችን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫ ላይ የተነሱ ዋና ዋና ሐሳቦች እንደሚከተለው ቀርቧል።
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2ዐ16 ዓ.ም በጀት አመት ያከናወናቸው ስራዎች ውስጥ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ንጽህ ስፖርት ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በማከናወን በበጀት ዓመቱም ውጤታማ እንቅስቃሴዎች ማካሄዱ ተገልጿል።
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2ዐ16 ዓ.ም በጀት አመት ያከናወናቸው ስራዎች ውስጥ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ንጹህ ስፖርት ለማስፋፋት የስፖርቱ ማህበረሰብ የግንዛቤ ለማሳደግ አጫጭር እና የገጽ ለገጽ ስልጠናዎችን በመስጠት 4372 የሚሆኑ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉን እና በህዝብ ንቅናቄ ዘመቻ ለማዳረስ 24323 ተሳታፊዎች በአወትሪችንግ ኘርግራም እና በህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራም እንዲሁም በየስልጠና ማዕከላት በመገኘት የማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር እንደተቻለም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
በሌላም በኩል በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ተካቶ በዶፒንግ ዙሪያ በቂ የሆነ እውቀትና ግንዛቤ የሟሟላት ሥራ የተሰራ በመሆኑ በበጀት ዓመቱም ውጤታማ ሥራ መሰራቱ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በ2016 በጀት አመት በአበረታች ቅመሞች የምርመራና የቁጥጥር ሥራዎች 744 ምርመራዎች የተደረጉ ሲሆን በአብዛኛው የኦሊምፒክ ተሳታፊ ስፖርተኞች ሲሆኑ በአጠቃላይ ከተደረጉት ምርመራዎች ወደ 6 የሚሆኑ በአበረታች ቅመሞች ተጠቅመው የህግ ጥሰት የፈፀሙት በመሆናቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸው ከባለፈው ዓመት ሲነፃፀር በ50% መቀነሱን ተናግረዋል።
በተያያዘም በኢንተለጀንስ ኢንቨስቲጌሽን ስራዎችን ከአትሌቶች ጀርባ ያሉ አካላት በተለያየ ደረጃ የበኩላቸው ተሳትፍ እንዳላቸውና በ2016 በልዩ ሁኔታ ኢንተለጀስ እና ኢንቪስቲግሽን ስራዎች አጠናክረን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ወደ 21 ኦኘሬሽኖች ከተሰሩት ስራዎች 7 ግለሰቦችና ተቋማት የተረጋገጠ በመሆኑ 3 የህክምና ባለሙያዎች፣ 1 አሰልጣኝ፣ 2 የህክምና ተቋም እና 1 ፈርማሲ የተሳተፊበት በመሆኑ አስፈላጊው እርምጃ የተወሰደ ሲሆን በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር ስራዎችንን አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመግለጫቸው ጠቁሟል።
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተቋማዊ አቅምን ለማሳደግ ትኩረት አድርጎ እየሰራ በመሆኑና አስፈላጊውን ግብአቶችን የማሟላት እና የአሰራር ስርአትን በማጠናከር በ2ዐ16 ዓ.ም በጀት አመት አመርቂ ሥራ መሰራቱን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል መግለጫውን ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል ፡፡
የዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ(ዋዳ) ባስቀመጠው አሰራር መሰረት በፓሪስ በሚካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለሚሳተፉ 160 በላይ አትሌቶች በምርመራ ቋጥ ውስጥ በማስገባት በልዩ ሁኔታ ከ8 እስከ 9 ጊዜ ምርመራ ከስታንዳርዱ በላይ በመስራትና መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ በማድረግ እና ስፖርተኞቹ ከአበረታች ቅመሞች የጸዱና ነፃ ሆነው እንዲወዳደሩ የቅድመ ከክትትልና ቁጥጥር ስራው በተጨማሪ ለአትሌቶች የአበረታች ቅመሞችን አስመልክቶ የግንዛቤ መፍጠር ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም በዚህ ዓመት በልዩ ሁኔታ እየሰራ ያለነው ሀገራችን የአድቫይዘር ግሩኘ አባል በመሆኗ ትልቅ እድል የፈጠረ በመሆኑና በአለም አቀፍ ደረጃ በሚሰሩ ሥራዎችን ኢትዮጵያ ሀሳቦች የምታቀርባቸው ሁኔታ ተፈጥሯ ብለዋል ።
ሀገራችን ውስጥ በአጠቃላይ በፀረ አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ባስመዘገብናቸው ውጤቶች ተቋሙ ባለው ትልቅ አቅም ደረጃ የተመረጠ በመሆኑ እንደ አፍሪካ ኢትዮጵያን ተወካይ ሀገር በመሆን የአድቨይዘር ግሩፕ ሥራዎች ሲሰራ የቆየበት ሁኔታ እንደነበር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመግለጫቸው ጠቁሟል።