ወ/ሮ ፋንታዬ አክለውም ጽ/ቤታችን የምገባ ፕሮግራሙን ሲደግፍ የተጣለበትን ማሀበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ካለው ብርቱ ፍላጎት አንጻርም እደሆን አበራርትተዋል፡፡
በተለይ በአትሌት ኮማንደር ደራቱ ቱሉና በአትሌት አልማዝ አያና የተደረገው እገዛ መልካምና አኩሪ ተግባር ነው፡፡ለሌሎች የስፖርቱ ቤተሰብ አራዓያ አደሆን ተናግረዋል፡፡
ም/ዋና ዳይሬከተር አያይዘው እደገለጹት በኮረና ወረርሽን ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአትሌቶች የዶፒነግ ምርመራና ቁጥጥር እንደሚጀመር አስታውቀው፤አትሌቶች የኮረና ቫይረስ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመከተል፤እራሳቸውን ከዶፒንግ እዲያርቁ አሳስበዋል፡፡
ፕሮግራሙን በይፋ ያስጀመሩት የኢፌድሪ ሰፖርት ኮሚሽን ከሚሺነር አቶ ኢሊያስ ሽኩርና ሌሎች ከፍተኛ መንግስት ባለሰልጣናት ናቸው፡፡
የምገባ ፕሮግራሙ የጠቅላይ ሚኒሰተር ክብር ዶ/ር አብይ አህመድ መዕድ መጋራት እኒሼቲፍ አካል ነው፡፡