በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን /IAAF/ የአትሌቶች ኢንቲግሪቲ ዩኒት /AIU/ ወይም ከውድድር ጊዜ ውጭ የአትሌቶች የዶፒንግ ምርመራ ክፍል የሥራ ኃላፊ የሆኑት ራፋኤል ሩክስ በኢትዮጵያ ብ/ፀ/አብ/ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተው የስፖርት አበረታች ቅመሞች /ዶፒንግን ለመከላከል እየተደረገ ስላለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል እና ከባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የውይይቱ ትኩረት በኢትዮጵያ የስፖርት የፀረ-አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ኘሮግራም እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴ ዙሪያ የተመለከተ ነው፡፡

በተለይ ጽ/ቤቱ በውድድር ጊዜና ከውድድር ጊዜ ውጭ የሚያካሂደውን የዶፒንግ ምርመራ ኘሮግራም እንቅስቃሴ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመቀጠልም በምርመራ ወቅት የናሙና አሰባሰብ ሂደት ምን እንደሚመስል የመስክ ላይ ምልከታ /Obserbation/ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል የETH-NADO እና IAAF እ.ኤ.አ በ2019 ለሚካሄደው የኳታር ዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዝግጅት የዶፒንግ ቁጥጥር ኘሮግራምና ንፁህ ስፖርትን ለማጠናከር ከወዲሁ ተቀራርበው በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በውይይቱ መጨረሻ ላይ ጽ/ቤቱ የዶፒንግ ቁጥጥር ኘሮግራም ለማካሂድ ተግዳሮቶች እንዳሉበት ተገልጿል፡፡ በተለይ ናሙናዎች መሰብሰቢያ ቁሶች /Kits/ እና የተሰበሰቡ የደም ናሙናዎች ወደ ላብራቶሪ ማጓጓዣ ትራንስፖርት እና ሌሎች የግብዓት እጥረት እንዳሉበት በውይይቱ ተመልክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *