የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ የቀጣይ የ6 ወር የዕቅድ ዝግጅት ኦረንቴሽን ተሰጠ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን በ2014 በጀት ዓመት በ6 ወራት ውስጥ የዕቅድ አፈጻጸም ገምግሞ የቀጣይ የ6 ወር የዕቅድ ዝግጅት ኦረንቴሽን ለተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ሰጥቷል፡፡
የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ በባለስልጣኑ በመንፈቅ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣ በትግበራ ወቅት የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን መለየት ከዚህም በመነሳት የወደፊት አቅጣጫን ማመላከት እንደሆነ በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል ገልፀዋል፡፡
የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ስረጉት በየነ፣ባለስልጣኑ በመንፈቅ ዓመቱ ያከናወናቸው ሥራዎች በሚዛናዊ ስኮር ካርድ መሰረት መለካቱን በመጥቀስ፣ የተከናወኑ ሥራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል ፡፡ በወ/ሮ ስረጉት በየነ እንደተብራራው፣ በበጀት አመቱ ሰፊ ስራ የተከናወነበት እደነበረ በዋናነት የትምህርት፣ ስልጠና እና የህዝብ ንቅናቄ፤ የምርመራና ቁጥጥር፤ አለም አቀፍ ግንኙነቱን የማጠናከር ፤የህግ ማዕቀፎችን የማዘጋጀትና ወደ ትግበራ የማሸጋገር እንዲሁም አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ተካትተው እንዲሰጡ ለማስቻል በየእርከኑ የቅድመ ዝግጅት ትግበራ ትኩረት ተሰጥቶ የተከናወኑ ስራዎች መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል የመድረኩን ማጠቃለያ አስመልክተው እንዳሉት ባለስልጣኑ በአለም አቀፍ ህጎችና የአሰራር ስርዓቶች መሰረት የእለት ተዕለት እንቅስቃሴውን የሚያካሂድ ከመሆኑጋር ተያይዞ የተቋሙን ተልዕኮ በብቃት እና በውጤታማነት ለመፈፀም ባለሞያውም ኃላፊውም የአለም አቀፍ ህጎችንና ስታነደረዶች ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።’’
አያይዘው ዋና ዳይሬክተሩ እደተናገሩት ’’ ከሰው ኃይል አንፃር ወደኳሊቲ (Quality) መምጣት አለብን፤ በተሠማራንበት የሥራ መስክ ብቃት ያለው (competent) ባለሞያ ሆኖ መገኘት ይጠበቅብናልን ፣ ስለዶፒንግ በሚገባ መናገር፣ማስረዳት መቻል አለብን፣ በዚህ ደረጃ ነው እራሳችንንም ፣ ተቋማችንም መገንባት ያለብን ብለዋል ፡፡’’
የተቋሙ አደረጃጀት እደገና መቀየር አለበት ፤ ከመንግስት በወረደው አዲስ አደረጃጀት ጋር ተስተካክሎ እደሚዋቀር ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በበኩላቸው በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የተገኙ ውጤቶችን በማስፋት ክፍተቶችንም በመሙላት በቀጣይ ልንሰራ እንደሚገባ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡