በአዲሲቷ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ውስጥ በሚገኘው ሀገረሰላማ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ አትሌቶች እና አሰልጣኞች በዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
(ETH-NADO መጋቢት 15/2013 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከ40 ለሚበልጡ በሀገረሰላም ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ አትሌቶች እና አሰልጣኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡
በስልጠናው ፕሮግራም ላይ ተግኝተው ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ እንደተናገሩት በአገራችን ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጣር ጽ/ቤታችን በስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡ የስልጠና መድረኮችን በማዘጋጀት የስፖርተኞችን ግንዛቤ ማሳደግ ለአገሪቱ ስፖርት እድገት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል ፡፡
ስፖርተኞች እራሳቸውን ከዶፒንግ በመጠበቅ ከሚደርስባቸው የጤና እና ተያያዥ ችግሮች ከፍም ሲል የሀገራቸውን ገጽታ ከሚያጉድፍ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ መጠንቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡ የዚህም ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዋና ዓላማ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ በመሆኑ በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል ፡፡
ስልጠናው በትምህርት እና ስልጠና ባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን በዶፒንግ ምንነት፣ ህግ ጥሰት፣የአትሌቶች መብትና ግዴታ፣ የዶፒንግ የምርመራ ሂደት እና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡:
በተያያዘም ዜና በኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ቦሬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የጽ/ቤቱ ምክትል ዳሬክተር እና ባለሙያዎች ከማሰልጠኛ ማዕከሉ ዳሬክተር ከአቶ ከላላ ሲዳ ጋር ውይይት አርገዋል፡፡
በማሰልጠኛ ማዕከሉ ላይ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ለአትሌቶቹ ከስልጠና ማኑዋሎቻችው ጋር አቀናጅቶ መስጠትና የሁልጊዜ አጀንዳ በማድረግ የተተኪ አትሌቶችን እውቀት በሚያሳድጉባቸው መንገዶች እንዲሁም በቀጣይ ከጽ/ቤቱ ጋር ተቀናጅቶ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ በስፋት ተወያይተዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *