በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም በዶፒንግ ዙሪያ ለስፖርት ክለብ አመራሮች፣የቴክኒክ ኃላፊዎች እና አሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው ፡፡
ሀሙስ ሚያዚያ 28/2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ከተለያዩ የስፖርት ክለብ ለተወጣጡ አመራሮች፣የቴክኒክ ኃላፊዎች እና አሰልጣኞች የፀረ-ዶፒኒንግ ግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የመድረኩ ዋና ዓላማ በየደረጃው የሚገኙ የክለብ አመራሮች፣የቴክኒክ ኃላፊዎች እና አሰልጣኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የጋራ ግንዛቤ በመጨበት በአገር አቀፍ ደረጃ ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ኃላፊነቶች መወጣት እዲችሉ የተዘጋጀ የጋራ የውይይት መድረክ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በመግቢያ ንግግራቸው የዛሬው የውይይት መድረክ አቅም የመፍጠርና ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ካሉ በኋላ ዶፒንግ በአሁን ወቅት ትልቅ አለም አቀፍ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የክለብ አመራሮች፣የቴክኒክ ሃኃላፊዎችና አሰላጣኞች ሚና ትልቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስለሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እደሚወጡ ያላቸውን እምነት በመግለፅ ተቀናጅተን በጋራ በመስራት የስፖርቱ ስጋት በመሆን ላይ የሚገኘውን ዶፒንግ ከመሰረቱ ለመከላከልና ለመቆጣተር ትልቅ አቅም ይኖረናል በማለት መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠል በጽ/ቤቱ የትምህረት፣ሰልጠና ምርምር ዳሬክቶሬት የስልጠና ባለሞያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ፅንሰ ሃሳብ የውይይት ሰነድ ላይ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በገለፃቸውም በዶፒንግ ምንነት፣ የተዘረጉ የስራር ስርአቶች፤የህግ ጥሰቶች፤ በሚያስከትሉት ጉዳቶች፤በአትሌቶች መብትና ግዴታ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በሚሉ ዋና ዋና ሀሳቦች ላይ ዘርዘር ያለ ገለፃ አቅርበዋል፡፡
በዚህ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ውይይት መድረክ ከተለያዩ የስፖርት ክለቦች የተውጣጡ አመራሮች፣ የቴክኒክ ኃላፊዎች እና አሰልጣኞች በድምሩ 50 የሚሆኑ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ውይይቱ ከሚያዚያ 28-29 ቀን 2013ዓ.ም እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡
መድረኩ ከምሳ በኃላ የሚቀጥል ሲሆን በመርሃ ግብሩ መሰረት በቀረበው ሰነድ ላይ የቡድን ውይይት ይካሄዳል፡፡
በነገው እለት በፀረ-ዶፒን የህግ ማዕቅፍ እና በስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች( Supplements)) ላይ ስልጠና ይሰጣል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *