ለክልልና ከተማ አስተዳደር ተወካዮች የፀረ-ዶፒኒንግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
**********************************************
ጥቅምት 24/2013 ዓ፣ም፡-
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH-NADO/ ከ30 ለሚበልጡ ለክልልና ከተማ አስተዳደር ተወካዮች የፀረ-ዶፒንግ ስልጠና በአዳማ ከተማ መሰጠት ጀመር፡፡

በስልጠና መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደርጉት የጽ/ቤቱ ም/ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋነታዬ ገዛኽኝ እደተናገሩት ስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ የአገራችን ስፖርት ዋና ተግዳሮት በመሆን ላይ እሆን ከመምጣቱ አንፃር፤ በተለይ በቀደምት ጀግኖች አትሌቶቻቸን የተገንባዉን የአገራችንን መልካም ገፅታ ለማስቀጠል፤ ጤናማ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ፍታዕዊ ውድድር መድረክ ለመፍጠር ፤የኢፌድሪ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥጥቶ ዘርፈ-ብዙ ጥረቶች በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጽ/ቤቱ በሚኒስተሮች ምክር ቤት በአዋጅ ከተቋመበት ጀምሮ በየደረጃው ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን ያከናወነ መሆኑን፤ በአጭር ጊዚያትም አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ እደተቻልም ም/ዋና ዳይሬክተሯ አብራርተዋል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ በክልል ደረጃ የፀረ-ዶፒነግ ጉዳዮችን በባለቤትነት የሚመራ አካል በማስፈለጉና በስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማት ካሪኩለም ውስጥ አካታች መስራት ስለሚገባ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በፌድራልና በክልል ደረጃ ባሉት ጥንካሬዎችና ድክመቶችላይ የጋራ መንገዳችን ቀይሰን የምንወያይበት መድረክ ጭምር እደሆንም ም/ዋና ዳይሬከተሯ ገልፀው ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የግንዛቤ ማሰጨበጫው የተካሄደው በዶፒንግ ምንነት፤ የህግ ጥሰት፤መርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ የዶፒንግ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶች እና በሚያሰከትሉት ጉዳቶች ላይ ያተኩረ ነው፡፡

ስልጠናው በጽ/ቤቱ የትምህርት፤ስልጠናና ጥናትና ምርመር ዳይሬክቶሬት ባለሞያዎች ገለጻ ተደርጓል ፡፡ በቀረበው የስልጠና ሰነድ ላይ የበቡድን ውይይት እተደረገበት ነው፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *