ለድሬደዋ ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ስልጠና ተሰጠ
ህዳር 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለድሬደዋ ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ አበረታች ቅመሞች/ዶፒንግን በመከላከልና በመቀጣጠር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ የሥልጠናውን መድረክ ሲያስጀምሩ እዳሉት ስለአበረታች ቅመሞች ምንነት፣ አሰራሩን፣ ህጉን ማውቅና ተግባራዊ ማድረግ እደሚያስፈልግ ገልፀው፡፡
አትሌቶች ሳትዘናጉ እራሳቸውን ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጠብቁ፤ በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ተጠቅሞ በማጭበርበር ማምለጥ አይቻልም በማለት አሳስበዋል፡፡
በሰልጠናው መድረኩ ላይ አትሌቶች፣የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞችን ተሳትፈዋል፡፡







