ስፖርተኞችን ከማሰልጠን ጎነ ለጎን ስፖርቱ እና ሰፖርተኞች ከዶፒንግ ችግር ነፃ የሚሆኑበትን ስራዎችን ሊሰራ እንደሚገባ የኢትዮጲያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ተናገሩ ፡፡
(ህዳር14/ 2014 ዓ.ም ሐዋሳ) የኢትዮጲያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኔስቴር በጋራ በመሆን በደቡብ ብሔር ብሔርስቦችና ህቦች ክልል እና ከሲዳማ ክልል በአትሌቲክስ፣ባህል ስፖርት፣ ቅርጫት ኳስ እና ጠረጴዛ ቴንስ በመጀመሪያ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና ለሚከታተሉ ስፖርት ሳይንስ መምህራን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የስፖርቱን ዘርፍ ከማልማት እና ስፖርተኞችን ከማስለጠን ጉን ለጎን ከዶፒንግ ችግር ስፖርተኞች ነፃ መሆን እንዲችሉ በስፋት ሰራዎቸን መስራት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
አያየዘውም ስፖርቱን ከተጋረጠበት አደጋ ልንጠብቀው ይገባል ለዚህም በየዘርፉ ስፖርትኞችን ስታሰለጥኑ እና ስታበቁ የዶፒንግን ጉዳይ በማካተት በማስተማር ግንዛቤ በመፍጠር በሰፖርቱና በስፖርተኞች አልፎም ተርፎ በሀገር ላይ ከሚከሰቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መጠበቅ ዋነኛ ስራችሁ ልታደርጉ ይገባልም ሲሉ ለመድረኩ ተሳታፊዎች መልዕከታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የስፖርት መምህራን ዶፒንግን ለመከላከልና ንፁህ ስፖርት ለማስፋፋት በሚደረገውን ጥረት ላይ ግንዛቤ ይዘው ስፖርተኞች በዶፒንግን ጉዳይ ላይ ማስተማር እንዲችሉ አቅም ለማጎልበት ዓላማ ያደረገ መድረክ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በስልጠናው ላይ ከሲዳማ ክልል እና ደቡብ ክልል ከተለያዩ ት/ቤቶች የተወጣጡ 125 የሚጠጉ የሁለተኛ ደረጃ የስፖርት መምህራን ተሳትፈዋል፡፡
በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ታሪካዊ አመጣጥ፣በሚያስከትላቸው ጉዳቶች፣የዶፒንግ ህግ ጥሰት እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለሰልጣኞች ገለፃ ተደርጓል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *