# ከዶፒንግ የጸዳ ስፖርተኞች እናፈራለን በሚል መሪ ቃል ለእግር ኳስ ክለቦች እየተሰጠ ያለው የጸረ አበረታች ቅመሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ፕሮግራም እንደቀጠለ ነው ፡፡
( ግንቦት 11/2013 ዓ.ም ሐዋሳ ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH_NADO/ ለአንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ እና ለሀዲያ ሆሳህና እግርኳስ ክለብ ቡድን ተጫዋቾች አሰልጣኞች እና የህክምና ባለሙያዎች በዶፒንግና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በሌዊ ሪዞርት አዳራሽ እና ክፍለ ሰላም ሆቴል አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
በስልጠና መድረኩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርአት ላይ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዳሉት ጽ/ቤታችን ከተቋቋመ 4 ዓመት ያስቆጠረ መሆኑን ጠቁመው በአሁን ወቅት የዶፒንግ ጉዳይ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ስፖርቱ ባለበት ሁሉ የሚኖር በመሆኑ ይህን ግንዛቤ መያዝ በጣም ጠቃሚ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡
የዚህም የስልጠና ዋና ዓላማ በዶፒንግና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ በስፖርቱ ላይ ሊደርሱ የሚችሉትን ችግሮችን ለመከላከል እንዲያስችል የታስበ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ ትምህርትና ስልጠናው ጨምሮ የምርመራና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ም/ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸው፤ ክለቦቹ ስልጠናው እንዲሰጥ ፍቃደኛ መሆናቸውና ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ የተዘጋጀውን ትምህርት በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበው መድረኩን አስጀምርዋል፡፡
የዛሬ ስልጠና በሁለት መርሃ ግብር ተከፍሎ የተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ (ሰባ) 70 ያህል ስፖርተኞች ስልጠናዉን ተከታትለውታል፡፡
ስልጠናው በትምህርትና ስልጠና ዳሬክቶሬት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መስረታዊ ጉዳዮች፤ በየደረጃው ባሉ የአሰራር ስርዓቶች እና አደረጃጀቶች ፤ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ በተከለከሉ የስፖርት አበረታች ቅመሞችና ዘዴዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው።
በቀጣይ ቀናት ለሌሎች ክለቦች ስልጠናው መሰጠቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *