ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ሰራተኞች ’’በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል’’ ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH-NADO/የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል የተዘጋጀ ሲሆን ሥልጠናው ለጽ/ቤቱ ሰራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ስልጠና ነው፡፡
ሥልጠናውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ መልዕክት በማስተላለፍ በይፋ ከፍተውታል ።
ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች በሥነምግባርና በሞራል ዕሴቶች ግንባታ፣በሙስና ወንጀል ሕጎች፣በሀብት ምዝጋባ፤ በሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ክፍል ስልጣንና ተግባር፣ የስራ ስነ-ምግባር ምንነት፣ ሙስናን በጋራ መከላከል በሚቻልበት መንገድ ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ የተዘጋጀ ስልጥና ነው፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ፣በዛሬው ዕለት፣ በሀብት ምዝጋባ፤ በሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ክፍል ስልጣንና ተግባር፣ የስራ ስነ-ምግባር ምንነት፣ ዙሪያ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣በሥልጠናው ላይ የፌድራል ስፖርት ኮሚሽን የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አያሌው እንዲሁም በጽ/ቤቱ የሥነ ምግባር እና ፀረ-ሙስና ክፍል ባለሞያ በአቶ እግዳዉ መስፍን ሥልጠናውን እየሰጡ ሲሆን ሥልጠናው ከነሐሴ 14 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደሚቆይ ታውቋል፡፡
በሥልጠናው ላይ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ሥራ ሙስናን አስቀድሞ ለመከላከል፣ የጥቅም ግጭትንና ብልሹ አሠራርን አስቀድሞ ለመከላከል፣ ኃላፊነትን በመጠቀም የግል ጥቅምን የማካበት አሠራርን ለማስቀረት፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብትና ንብረት እንዳይፈራ ለመከላከል ጠቀሜታ ያለው መሆኑ ተጠቅሷል፡
ሙስና ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ ከመስራት ይልቅ ስልጣንና ኃላፊነትን መከታ በማድረግ ሕግን ጥሶ የመንግሥትና የህዝብ ሀብትና ንብረትን መስረቅ፣ መዝረፍ፣ ማጭበርበር እንዲሁም በጉቦ፣ በዝምድና፣ በትውውቅ፣ በጐሰኝነት፣ በፖለቲካ ወገንተኝነትና በኃይማኖት ትስስር ላይ በመመርኮዝ አድሏዊ በሆነ አሠራር ፍትህን እያዛቡ የግል ጥቅምን ማካበትና ሌላን ወገን ተገቢ ባልሆነ መንገድ መጥቀም እንደሆነ በርካቶች ይስማሙበታል፡፡በነገው ዕለት በሙስና ወንጀል ሕጎች፣በሥነምግባርና በሞራል ዕሴቶች ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ይሰጣል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *