በአዲስ አበባ ስታዲየም እየታካሄደ ባለው 50ኛው የወርቅ እዮቤልዩ የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ሻንፒዮና ውድድር ላይ ለተገኙ የስፖርት ማህበረሰቡ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማጎልበት የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨብጫ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (ETH-NADO) በአዲስ አበባ በሚካሄደው 50ኛው የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ሻምፕዮና ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ተተኪ ስፖርተኞች፣ የስፖርት ባለሞያዎች፣ የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ህክምና ባለሞያዎችንና የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና የፀረ-ዶፒንግ ንቅናቄ ፕሮግራም በሰፊው በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የህትመት ውጤቶች ፤ በአማርኛ ቋንቋ እና በኦሮምኛ የተዘጋጁ ብሮሽሮች እየተስራጩ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አስተማሪ መልዕክት የያዙ ባነሮች ተዘጋጅተው በየውድድር ስፍራዎች ተሰቅለዋል፡፡ በተጨማሪም በፕሮግራም መሪዎች አማካኝነት የተለያዩ በዶፒንግ ዙሪያ መልዕቶችን በየፕሮግራሙ መሀል በማስተላልፍ ግንዛቤ ለመፍጥር ተቸሏል፡፡
ውድድሩ ከመጋቢት 28-ሚያዚያ 03/2013 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል፡፡
ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ነፃ ቀን ለፍትኃዊ የስፖርት ውድድር እና ለስፖርተኞች መብት መከበር !!! # Play True Day Campaigns, 2021 በታዋቂ አትሌቶች ንቅናቄን ለመፍጠር ተችሏል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *