በስፖርቱ ውስጥ በኃለፊነት፣ በአሰልጣኝነት እና በመሳሰሉት ሙያዎች እያገለገሉ ያሉ ባለሞያዎች ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋትና የአትሌቲክሱን መልካም ገፅታ ለማስቀጠል በሚደረገው ርብርብ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እደሚጠበቅባቸው ተገለፀ፡፡
በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በክልልና ከተማ አሰተዳደር ስር ለሚገኙ በአገር አቀፍናና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚወዳደሩ ለማርሻል አርትስ ስፖርት እና ለጂምናስቲክ ፌድሬሽን አመራሮችና አሰልጣኞች ግንዛቤ ለማጎልበት ለተከታታይ 2 ቀናት በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የቆየሁ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ በወንጀል ህጉ እና የኢትዮጵያ ፀረ-ዶፒንግ የሕግ ማዕቅፎች የመጀመሪያ ረቂቅ ሰነድ ላይ ሲፊ ገለፃና ወይይት ተደርጎበታል፡፡
በመድረክ ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ም/ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እደገለፁት በስፖርቱ ውስጥ በኃለፊነት፣ በአሰልጣኝነት እና በመሳሰሉት ሙያዎች እያገለገሉ ያሉ ባለሞያዎች ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋትና የአትሌቲክሱን መልካም ገፅታ ለማስቀጠል በሚደረገው ርብርብ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እደሚጠበቅባቸው ተገለፀ፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም አገር አቀፍ ፌድሬሽኖችና የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት ’’የዶፒንግ ጉዳይ’’ በስልጠና ማኑዋል ውስጥ አካተው ማስተማር እደሚጠበቅባቸውም ገልፀዋል፡፡