ከተለያዩ የሙያ ዘርፍ ለትውጣጡ ረዳት የዶፒንግ የምርመራና ቁጥጥር ሰልጣኝ ባለሙያዎች የእውቀትና የክህሎት ሽግግር ስልጠና መስጠት ተጀመረ::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የተሰጠውን ተልዕኮ በዕውቀት ለማስፈፀም ያስችለው ዘንድ ከተለያዩ የሙያ ዘርፍ ለተውጣጡ ረዳት የዶፒንግ ምርመራ እና ቁጥጥር ባለሙያዎች የዕውቀት እና የክህሎት የሽግግር ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ ራስ ሆቴል ከጥቅምት 19 – 21/2012 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ለቀናት የሚቆይ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ስልጠናው (የዕውቀት ሽግግሩ) በዋናነት የሚያተኩረው በዶፒንግ ምንነት እና ሙያዊ ቃላት፣ ምርመራ እና ኢንቨስትጌሽን፣ የባለሙያው መብት እና ኃላፊነት (General rules on filling)፣ ማጀብ (Athlete notification and escorting) ከስፖርት አበረታች መድሓኒቶች ጋር በተያያዘ በሚያስከትሉት የጎንዮሽ ጉዳቶች ፣ የረዳት ባለሙያዎች ኃላፊነት እና ተግባር ፣ ቅፅ አሞላል እና Notification of athlete and witnessing በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ነው፡፡


ስልጠናውን አጭር ንግግር በማድረግ የከፈቱት ወ/ሮ ፋንታዮ ገዛኸኝ የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ ሰልጣኞች በስልጠና ያገኙትን ዕውቀት የመተግበር ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመጨራሻም ም/ዋና ዳይሬክተሯ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት መከታተል እንዳለባቸው መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *