የኢትዮጵያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባባር ለስፖርት ሳይንስ መምህራን እና ተማሪዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዛሬው ዕለት አካዷል።
(ግንቦት/02/2014 ዓ.ም) የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት ዶ/ር የማነ ንጉሴ የስፖርት ሳይንስ ዳይሬክተር ሲሆኑ አገራችን በአትሌቲክሱ ብዙ ዕንቁ ልጆችን አፍርታለች እነዚህ አትሌቶች ሲሮጡ ተፈጥሮ በሰጠቻቸው አቅም ተጠቅመው ነው ነገር ግን አሁን አሁን ከሌሎች በልጦ ለመገኘት ስፖርታዊ ስርዓቱን በጣሰ መልኩ ለማካሄድ ሲሞከር ይታያል ይህንንም መታገል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በሌላም በኩል ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ አካዳሚ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው እናንተ ወደፊት በስፖርቱ ላይ በተለያዩ መልኩ የምትሳተፉ እና ስፖርተኞችን የምታበቁ በመሆናችሁ በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤያችሁን በማሳደግ በስፖርቱ ላይ ትልቁን ድርሻ እንድትወጡ ለማስቻል ዓላማ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ዶፒንግ ለጊዜው የሚጠቅም የሚመስል ነገር ግን በአትሌቶች ህይወት ላይ እና አጠቃላይ በስፖርቱ ላይ የሚኖረንን ቆይታ የሚያሳጥር መሆኑንንም ጠቁመዋል ::
ስልጠናው በተቋሙ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

By Ermias