የምስራቅ አፍሪካ አገሮችና የአፍሪካ ዞን 5 የፀረ-ዶፒንግ ድርጅት አባል አገራት መደበኛ የፀረ-ዶፒንግ ስብሰባ በአገራችን አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል፡፡

ቀን፡ ሰኔ 03/2011 ዓ.ም

አገራችን ኢትዮጵያ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመከላከልና በመቆጣጠር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት በየደረጃው ዘርፈ-ብዙ ጥረቶችን እያደረገች መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ዓመት የሚካሄደውን የምስራቅ አፍሪካ አገሮችና የአፍሪካ ዞን 5 የፀረ-ዶፒንግ ድርጅት አባል አገራት መደበኛ የፀረ-ዶፒንግ ስብሰባ ታስተናግዳለች፡፡

ስብሰባው በአዲስ አበባ ከተማ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ከሰኔ 5-6/2011 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በቀጠናው የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት ይመክራል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ስራውን እንዲሁም አለም አቀፍ ህጎችንና የአሰራር ስርዓቶችን በጠበቀ መልኩ በመንቀሳቀስ ረገድ የአገራችን ተሞክሮዎች ተቀምረው ለሌሎች አገሮች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

በዚህ ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ አገራትም ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል፡፡

Previous post የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከሁሉም ክልሎች/የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ከ500 በላይ ለሚሆኑ የስፖርት ባለሞያዎች(አሰልጣኞች፣ ዳኞች እና ኢንስትራክተሮች) በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ መስጫ ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
Next post የክብደት ማንሳት ስፖርተኞች በ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ለመሳተፍ የአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራ የአድራሻ (Whereabouts Information) ምዝገባ ማካሄድ ሳይችሉ ቀርተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.