የሴቶችን አቅም በማሳደግ ወደ መሪነት ማምጣት ይገባል ተባለ፡፡
የኢትዮጲያ የጸረ – አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የሴቶች ፎረም 1ኛ ዓመት በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል፡፡
(ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም አዳማ) የውይይት መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የኢትዮጲያ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዩ ገዛኸኝ ሲሆኑ የእራሳችንን አቅም በመፍጠር ያሉብንን ተግዳሮቶች በማሽነፍ ወደፊት መውጣት የእኛ የሴቶች አላፊነት ነው ብለዋል ፡፡
የውይይት መድረክ ዓላማ ሴቶች አትችሉም የሚሉትን አሉታዊ አስተሳሰቦችን በማሽነፍ እራሳሳችንን የምናበቃበት ፣ መብትና ግዴታችንን የምንወጣበት እና በመደጋገፍ በህይወታችን የሚገጥሙን ተግዳሮቶች ማሽነፍ እንድንችል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አያይዘውም ተቋማችን ሴቶችን ለማብቃት ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ተናግረው በተለይም ወደተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ ሴቶችን የማምጣት ስራ ዋነኛው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እና የጾታ እኩልነትን ከማስገኘት አኳያበአገራችን አሁንም ብዙ ሥራ እንደሚቀር ገልጸው በመሆኑም በአካልም ሆነ በመንፈስ የበቃችሁ ልትሆኑ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
በዛሬውም ዕለት የህይወት ክዕሎት ስልጠና ፣ የኤች አይ ቪ ኤድስን እና ኮሮና ቫይረስ እንዴት መከላከል ይቻላል ፣ የሴቶቸ መብት በቤተሰብ እና በወንጀል ህግ ምን ይመስላል ፣ የሴቶች ፎረም የ2013 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸምና የ2014 ዓ.ም ዕቅድ እንዲሁም የፎረሙ መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ በአባላቱ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡
አጠቃላይ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ሴት ሰራተኞች በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ሲሆን ፕሮግራሙ በነገውም ዕለት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
May be an image of 4 people, people sitting, people standing and indoor
May be an image of 1 person, sitting and indoor
May be an image of 3 people, including Birhane Abebie, people sitting, people standing and indoor

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *