የባለሙያዎችን አቅም በተሻለ መንገድ እየገነቡ መሄድ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ወሳኝ እንደሆነ ተጠቆመ ።
ለዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባልሙያዎች ሲሰጠ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ፕሮግራም ተጠናቅቋል።
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ያለፉትን አስቸጋሪ ጊዜያት ተቋቁመን የአለም አቀፉን የአሰራር ስርዓት በመከተል ኦሎምፒክና የአለም ሻምፒዮናዎችን ጨምሮ በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በተገቢው ሁኔታ መሳተፍና ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል። እነዚህን ስኬቶች እንድናስመዘግብ በበጎ ፈቃደኝነት የሚሳተፉ የምርመራ ባለሞያዎች (Sample Collection Personnel)ሚና ከፍተኛ እንደነበረ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ባለሙያዎቻችን ምስጋና ይገባችዋል ብለዋል፡፡
አያይዘውም በቀጣይ ትኩተት ተሰጥቶባቸው ሊሰራባቸው የሚገቡ ኃሳቦችን ያነሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በምርመራ ናሙና አሰባሰብ ወቅት የሚከሰቱ የአሰራር ግድፈቶችን ወይም Irregularity ትኩረት ሰጥቶ ሙሉ በሙሉ መቅረፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ከዚህም ባሻገር አለም አቀፍ የአሰራር ስርዓቶችን እና ህጉችን ጠብቆ መስራት አለመቻል እንደ አገር ብዙ ዋጋ ሊያስከፍል ስለሚችል በቁርጠኝነት መስራት አስፈላጊ እንደሆነም ገልፀዋል ፡፡
በቀጣይ የሙያተኞች የዕድገት መሰላል እንደሚዘረጋ የጠቆሙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ባለሞያዎች በዚህ ሂደት ውስጥ ለማለፍ በቁርጠኝነት እና ራስን በማብቃት ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አንስተዋል። በቀጣይም የባለሙያዎችን ብቃት በመለካት በእርከን የማሳደግ ስራ ሊሰራ የሚችልበትን አሰራር በመዘርጋት እንደሚተገብር አረጋግጠዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የሙያ ክፍያን በማጥናት ለመንግስት መቅረቡንና ለማስፀደቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጨረሻም ባለፉት ጊዜያት እንደ አጠቃላይ የነበሩን ስራዎቻችን ውጤታማ ነበሩ ያሉት አቶ መኮንን የነበሩብንን ክፍተቶች ደግሞ በማረም ከፊት ለፊታችን በቀጣይ የተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች የሚጠብቁን ስለሆነ ስራዎቻችንን በተሻለ መንገድ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *