ባለፉት ጊዜያት በአገራችን ኢትዮጵያ የስፖር አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተቋማዊ አደረጃጀቱን ማጠናከርን ጨምሮ የተካሄደው እንቅስቃሴ ውጤታማ በሆነ መልኩ መፈፀሙን የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አስታወቀ።
በአለም አቀፍ ህጎችና ስታንዳርዶች መሰረት በየደረጃው ጠንካራና ቀጣይነት ያለው የፀረ-ዶፒንግ ስርዓት ለመዘርጋት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ከአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) እና ከደቡብ አፍሪካ የፀረ-ዶፒንግ ተቋም ጋር የሶስትዮሽ የፓርትነርሽፕ ፕሮግራም በመቅረፅ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን የሚፈለገውን ስኬት ማስመዝገብ መቻሉን አፈፃፀሙ በተገመገመበት ወቅት ተጠቁሟል።
ይህ ውጤት በአፍሪካ ደረጃም ንፁህ ስፖርት ለማስፋፋት ከፍተኛ እንደሚኖረው ኤጀንሲው በድረ-ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።
ዝርዝር መረጃውን በሚቀጥለው Link ላይ ማግኘት ይችላሉ።