የአፍሪካ የፀረ-ዶፒንግ የፖርትነርሽፕ ፎረም የተካሄደ ሲሆን በፎረሙ ላይ አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ የሌሎችም የአፍሪካ አገራት ተወካዮች፣ የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) የስራ ኃላፊዎችና ሙያተኞች፣ የአሜሪካና የአውሮፓ አገሮች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።
በዚህ ፎረም ላይ የለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ፣ የኬንያ፣ የአለም አቀፉ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ (IPC) እና የሌሎችም ተቋማት ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በአሁኑ ወቅት አገራችን የደረሰችበት ደረጃም በፎረሙ ላይ በስፋት ተገልጿል።